ለእየሱስ አምላኪዎች ጥያቄ ~ የመሲህ ባሮች ሆይ - አንድ ጥያቄ አለን የተረዳው ካለ - መልሱን እንሻለን ጌታ ግፍ አቅቶት - ሰዎች ከገደሉት አለቀ አከተመ - የታል አምላክነት?! ሰዎች የሰሩትን - በሱ ላይ ሲያደርሱ ጌታ ግብራቸውን - ፈቅዶ ነው በራሱ? እንዲያ ከሆነማ - ምንኛ ታደሉ?! ፍቅሩን ይቸራሉ - ፈቃዱን ሲሞሉ። ባደረሱት ሁሉ - አልፎ ከተከፋ እንግዲህ ምን ይባል? ሀይሉ ከኮሰሰ - ሀይላቸው ከሰፋ?! ግን እንጠይቃለን - ለመልስ አትንፈጉ ማለባበስ ይቅር - ይመለስ በወጉ ፈጣሪዋን አጥታ - ዐለም ስትዋትት ሰው ወደ ማን ነበር - የሚያስበው ፀሎት? ፍጡር ፈጣሪውን - ካፈር ሲያደባየው ሰባቱን ሰማያት - ማነበር ያቆየው? ምስማር ተቸንክሮ - ሲያሸልብ ፈጣሪ ዓለም ቀርታ ነበር - ያለ አስተናባሪ? የሰማይ መላእክት - ምንኛ ለገሙ?! እጁ ተቸንክሮ - ዋይታውን ሲሰሙ? እንጨቱም ታምር ነው - አቅሙ መቋቋሙ አምላክ ያክል ነገር - ችሎ መሸከሙ ስለቱስ ጭቃኔው - ብረቱ ምስማሩ አካሉን ሰንጥቆ - ስቃይ ማሳደሩ ጉድ በሉ እሄን ጌታ - በአይሁድ የሚረታ ማጅራቱን ታንቆ - ታስሮ የሚመታ ኋላስ ራሱ ነቃ - ከሞት አንሰራራ ወይስ ጌታ አገኘ - ህይወት የሚዘራ?
Jan 01, 2025ጥያቄው መልካም ቢሆንም ቅሉ አስፍቶ ሚያይ አእምሮ ሊኖርህ ይገባል ካለዛ እንኳንስ የአምላክን ሰው መሆን ሚስጥር ይቅርና ቀላሏን ዘፍጥረትን ራሱ አይገለጥልህም ለማንኛውም የእኛ አምላክ የአለም ሁሉን ፈጣሪ የሚታየውን እና የማይታየውን አስገኝ በሶስት አካል አንድ አምላክነት ራሱን በገለጠው ልክ ምንቀበለው "ሁሉን ቻይ የሆነ ነው" የሌሎቹ አምላክ ተብዬያቸው ግን ሁሉን እንደማይችል ማሳየው እንዴት አምላክ እንዲህ ይሆናል ብለው ይጠይቁናል የሁሉን ቻይ ትርጉሙ ግራ የገባቸው ... ለማንኛውም በተብራራ መልክ ይገባህ ዘንድ አንድ ትምህርት በቪዲዮ ልላክልህ ከጠቀመህ ታተርፍበታለህ ሰላም ቆየኝ ክፍል ፩ https://m.youtube.com/watch?v=50sDIuQr2QM&t=105s&pp=ygWwAU1LIFRWIOGKkOGMiOGIqCDhiIPhi63hiJvhipbhibUgfHwg4Yid4Yi14Yyi4YioIOGIpeGMi-GLjCB8fCDhiqDhiJ3hiIvhiq0g4Yiw4YuNIOGLqOGIhuGKkOGJoOGJtSDhiJ3hiq3hipXhi6vhibV8fCDhiaDhiJjhiI3hiqDhiqgg4Yqg4Yit4Yur4YidIOGJgOGIsuGItSDhiaXhiK3hiIPhipEg4YyO4Ymg4YqT ክፍል ፪ https://m.youtube.com/watch?v=Nv5T5HQhlXU&t=21s&pp=ygWwAU1LIFRWIOGKkOGMiOGIqCDhiIPhi63hiJvhipbhibUgfHwg4Yid4Yi14Yyi4YioIOGIpeGMi-GLjCB8fCDhiqDhiJ3hiIvhiq0g4Yiw4YuNIOGLqOGIhuGKkOGJoOGJtSDhiJ3hiq3hipXhi6vhibV8fCDhiaDhiJjhiI3hiqDhiqgg4Yqg4Yit4Yur4YidIOGJgOGIsuGItSDhiaXhiK3hiIPhipEg4YyO4Ymg4YqT
Jan 01, 2025