Give me advice በሀገራችን ብዙዎቻቹ ታውቁታላቹ የቤተሰብ እምነት ምናምን እየተባለ ከድሮ የመጣ ነገር አለ እናም በእኔ ሀያቶች ውስጥ ነበር ። እናቴ ብዙም የለችበትም ነበር ነገር ግን እኔ ስወለድ እኔም እናቴም በጣም ታመምን እና እኔ ልሞት ነበር ከዛ ግን ወደ ትልቅ ሰዎች ጋር ሄዳ ምን ላድርግ ስትል የቤተሰብ ነገር አለብሽ እና ሄደሽ አመቺሳ አስነሺው ልጁን ተባለች ( ክርስትና ተነስቻለው) ማለትም ተጠምቄያለሁ ግን በጊዜው የነበርኩበት ሁኔታ አስጊ ስለነበር ይዛኝ ሄደች እና አመቺሳ ተነሳሁ ። እናም አደኩ ምናምን አሁን ሀያ አንድ አመት ሞልቶኛል ለእዛ ነገር ምንም ፍላጎቱ የለኝም መሄድም ምንም ማረግ ፍላጎት የለኝም ኦርቶዶክስ ነኝ እና እምነቴ አጥብቄ መያዝ እፈልጋለሁ ከሀጥያቴም ነፃ መውጣት እፈልጋለሁ ። ግን አሁን ከቤተሰብ ጋር ነው ምኖረው እና እነሱ ደሞ ያንን አይፈልጉትም ያ ትክክለኛው መንገድ እንደሆነ ነው ሚያስቡት እዛ እንድሄድ ምናምን ይፈልጋሉ እኔ ግን በጭራሽ ላረገው ማልፈልገው ነገር ነው በነገራችን ላይ ይሄ ነገር እናቴን ከስድስት አመት በፊት አሳጥቶኛል💔 እሷን መቅበር ሁላ አልቻልኩም ። እናትም አባትም ሁሉም ነገር ሆና ያሳደገችኝ እሷ ነበረች ። ምን ትሉኛላቹ ?
Dec 30, 2024የዚህ ነገር ጎጂነቱን እናትን የሚያህል ነገር ነጥቆ ካሳየህ ነገ አንተንም የቀረውንም ቤተሰብ ይወስድብሃል ስለዚህ በሀይማኖት በፆም በፀሎት በሱባኤ ግደለው በሀይማኖት ራስን አበርታ ንሰሃ ግባ መፅሐፍ ቅዱስ አንብብ በተለይ መዝሙረ ዳዊት አብዛኛውን ጊዜ ይመከራል ከአባቶች ቀረብ ብለህ ደግሞ ተማከር ትምህርቶችንም ተማር
Dec 30, 2024