ለክርስትና እምነት ተከታዮች ብቻ እስኪ ይሄንን ግጥም አይታቹ judge ሳታደርጉ አስተያየት ስጡኝ የባልንጀራ ትርጉም ከይሁዳ እያሪኮ ሳለሁ እየወረድኩ በወንበዴዎች ዱላ በዘራፊዎች እጅ ወደኩ መንገድ ዳር ተኝቼ ስል ከመች መች ሞትኩ አንድ ካህን ባጠገቤ ሲያልፍ አስተዋልኩ " እሰይ እሰይ የወገኔ ልጅ መጣ አሁን ነፃ ወጣሁ ከዚህ ሁሉ ጣጣ" ብዬ ተናግሬ ተመስገን እንዳልኩኝ ያ ያገሬ ልጅ የእስራኤል ካህን አይቶኝ እንዳላየኝ ሲያልፈኝ አየሁኝ ልቤ ስትሰበር ቁስሌም ሲበረታ አየሁ አንድ ሌዋዊ በመንገድ ሲመጣ "ይሄ ሌዋዊማ እኔ ላይ አይጨክንም በህይወት እና በሞት መሀል አይተወኝም" ብዬ ብጠባበቅ በፍፁም በተስፋ ይሄኛውም ሰው እንደዛኛው ካህን እኔን ጥሎኝ ጠፋ የደረቀውን ደሜን በእንባዬ እያራስኩ የሚረዳኝ አጣሁ እያልኩ አለቀስኩ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ደሜ ላይ ተኝቼ ያባቶቼ አምላክ ነፍሴን እስኪቀበል ከልቤ ጓጉቼ ድንገት ድምፅ ሰማሁ የፈረሶች ኮቴ አየሁኝ አንድ ሰው ያልሆነ ከበርቴ ከነቁስሌ አንስቶ ፈረስ ላይ ሲያረገኝ የዚህን ሰው ማንነት ለማወቅ ጓጓሁኝ እንደምንም..... ቀና ብዬ ሳየው ንቄ የጠላሁት ያ ሳምራዊ ነው ያ ደግ ሳምራዊ አጠበልኝ ቁስሌን ባልንጀራ ሆኖኝ ታደገኝ እኔን ትክክለኛ ትርጉም ፍቺ የባልንጀራ ጌታ እየሱስ ነው ለሰው የሚራራ
Dec 29, 2024Betam des ylal ewnet ❤️❤️
Dec 29, 2024