hi guys I have a question for christians.. ክርስቶስ ይቅር እንዳለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንድንል መፅሀፍ ቅዱስ ደጋግሞ ይነግረናል...እና ያ ይቅርታችን ገደቡ እስከየት ነው ሚለው አሳሰበኝ...አንድን ሰው እንደ ክርስቶስ ይቅር ካልን ድጋሚ እድል መስጠት አለብን ማለት ነው ምክንያቱም ክርስቶስ"ይቅር ብዬሃለው ከዚ በኋላ ግን ከኔጋ አትቀጥልም" አይለንም። ጥያቄዬ: የታዘዝነው ይቅርታ... እድል መስጠትንም ያካትታል ወይ?
Dec 27, 2024አንተ የጠየከውን ጥያቄ ጴጥሮስም ጠይቆት ነበር. . . ክርስቶስ ያስተማረን እንደ አባታችሁ ሁኑ ብሎ ነው አባታችን ደግሞ ለጻድቁም ለሐጥያተኛውም እኩል ፀሀይ ያወጣል. . . ሁሉም ይቅር በለኝ ቢለው ብዙ ነው የበደልከኝ ብሎ ለይቶ አልልህም አይልም. . . አንተም ይቅር ማለት ያለብህ እግዚአብሔር ላንተ ይቅርታ ባደረገበት ልክ ነው. . . እድል ላልከው አባታችን እድል አልሰጥም ቢል ኖሮ የሚፈጠረውን አስበኸዋል?? ለዛ ለኛ ይከብዳል ለእሱ ስለሚቻለው ለእግዚአብሔር ይሄን ልብ እንዲሰጥህ ለምነው. . . ጠባቧ በር ማለት ይህቺ ናት!
Dec 27, 2024