ሰላም እንዴት ናችሁ የAAU ተማሪ ነኝ ማርያምን እዚ ያለው ህይወት በጣም ከብዶኛል የክፍለሀገር ልጅ ነኝ መጀመሪያ እንደመጣሁ ከቤተሰብ ትንሽ ብርም ቢሆን ይላክልኝ ነበር ግን በቂ ብር አልነበረም ሚልኩልኝ ምክንያቱም የላቸውም በዛ መሀል ስራ አገኘሁ እና ብር አትላኩ ለራሴ አላንስም ብያቸው ያለፈውን አመት ከእ/ር ጋር በጥሩ ሁኔታ አሳለፍኩ ለራሴም እያብቃቃሁ ስችል ደሞ የሆነነገር እንዲያሟሉበት ለነሱም እየላክሁ በዚኛው አመት ግን ነገሮች የተገላቢጦሽ ሆኑብኝ 😢እንኳን እነሱን ላግዛቸው ለራሴም መሆን ከበደኝ ምሰራው ስራ ባጋጣሚ ቆመ ከዛ እቃዎችንም ግቢ ውስጥ ማሻሻጥ ምናምን ሞከርኩኝ አልተሳካም ይህን ያህል ከሰው ጋር connection የለኝም ከclass ጋር ማይጋጭ ስራ ፈለኩ ፈለኩ ግን ላገኝ አልቻልኩም 😔ምን አይነት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዳለሁ አታውቁም ሴት ነኝ ብዙ ነገሮችን ለራሴ ማሟላት ይጠበቅብኛል እነሱን ላኩልኝ ለማለት ደሞ ከባድ ነው እንደነገርኳችሁ የላቸውም ደሞ ያሉበት አካባቢ ግጭት ነው 😢 ብቻ ከብዶኛል በዚ የትምህርቱ ነገር አለ በዚ ቤተሰቦቼ ዛሬ ነገ በግጭቱ ምክንያት የሆነ ነገር ሆኑ እያልኩ አስባለሁ በዚ ደሞ ስራ አለማግኘቴ ሚያስፈልጉኝን ማሟላት አለመቻሌ ለነሱም የሆነ ነገር እንኳን አለማድረጌ ሰላም ይነሳኛል😔ብቻ ምን ልበላችሁ😢እና ሁላችሁም በፀሎታችሁ አስቡኝ ስራም እንዳገኝ ፀልዩልኝ አመሰግናለሁ 🙏
Dec 26, 2024ayzosh berchi keHone gize bewhala yehen post aytesh "ya hulu alefe" yasblesh—ayzon💪🏻
Dec 26, 2024