#አደራ እንዳታልፉት ሰላም ዉድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? ቀጥታ ወደ ጉዳዬ ስገባ የናንተን ምክር የሚፈልግ ጉዳይ ገጠመኝ። እሱም ምን መሰላችሁ እኔ የክፍለ ሀገር ልጅ ነኝ አሁን የምሰራዉ ግን አዲስ አበባ ነዉ። እና ቤተሰቦቼ ደግሞ ክፍለ ሀገር ናቸዉ ያን ያህል የኢኮኖሚ አቅም የላቸዉም። ስለዚህ ኦንደቤቱ የመጀመርያ ልጅነቴና ብቸኛ ስራ እንደያዘ ሰዉ እነሱን የመርዳት ሀላፊነት አለብኝ። ታዲያ እዚህ ቤት ኪራይ ከፍዬ ስፈ እነሱ ጋር ልኬ ስል ደሞዜ ከመምጣቷ ታልቃለች። ታዲያ ይህ በእንዲህ እንዳለ እናቴ ታምማ አዲስ አበባ የተሻለ ህክምና ያስፈልጋታል ተብሎ እዚ ልትመጣ ነዉ። እና እኔ ወንድማቹ ድሮም ብድር በብድር ሆኛለሁ በተለያዩ እዚ በማልገልፃቸዉ የቤተሰብ ችግሮች አሁን ለህክምና ኬት ላምጣ። አይደለም ለህክምና እዚህ ምትመጣበት የትራንስፖርት ብር እንኳን ምልክላት የለኝም። ግራ ግብት ቢለኝ ምን ማድረግ አለብኝ ብዬ ወዳናንተ መጣሁ። ቢያንስ በማታ የሚሰራ ትርፍ ሰአት ስራ ባገኝ ወይ የሆነ የምጠቁሙኝ መፍትሄ ካለ ብዬ። ብቻ አይምሮዬ ጧ ብሎ ሊፈነዳ ነዉ በጭንቀት ሰሞኑን ስራ ራሱ እንደድሮ መስራት አልቻልኩም። ብቻ የተሰማቹን ነገር በሉኝ ቢያንስ ለናንተ በመናገሬ ከቀለለኝ እና መፍትሄ ካገኘዉ ብዬ ፃፍኩት።
Dec 26, 2024Jesus brother thats my biggest fear, i wish i had some and help you yemr Idk what to do other than praying for you and your mother. Emebrhan tawtak hulun tastekaklkk
Dec 26, 2024