#religion mainly for Protestant ሌሎቻቹም ተሳተፉ ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው ብለን እንድንቀበል ያደረገን መፅሐፍ ቅዱስ ነው አይደል ምክኛቱም በግልፅ ስለተፃፈ 👉ሮሜ 8:34፤ ዕብ 7:24፤ ዕብ 5:7... መልካም በእነኚህ ጥቅሶች ክርስትስን አማላጅ ካልነው ኢየሱስ በዚው መፃፍ ላይ አብን አምላኬ እያለ ጠርቶታል 👉ዮሐ 20፡17 ስልጣኑም ከአብ ያገኘው እንደሆነና ሚያደርገውን ነገር ከአብ እንደተቀበለ ተናግሯል 👉ማር 10:18 ዮሐ 5:20 ዮሐ 6:57 ዮሐ 14:28 ኤፌ 1:3 2ኛ ቆሮ 1:3 1ኛ ጴጥ 1:3 ራዕ 3:15 የኔ ጥያቄ ከላይ ያየናቸውን ጥቅስ ይዘን ክርስቶስ አማላጅ ነው ካልን በእንኚህ ጥቅስ ደግሞ አብ የጌታ አምላክ ነው ወይ ደሞ አብ ወልድን ይበልጣል ማለት እንችላለን? 👉አማላጅ ለሚለው ትርጓሜ የለውም ከተባለ ለእነኚስ ለምን ትርጓሜ እንሰጣለን? 👉በመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ወልድን አማላጅ ያለ ትክክል ከሆነ ለምን አብ የወልድ አምላክ ነው ወልድ ከአብ ያንሳል የሚልም እውነተኛ አይሆንም ታድያ? 👉በዚው ኢየሱስ ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም ምትሉትም ማስረጃ ብትሰጡኝ ፨ሁላችሁም ተሳተፉ ግን በጨዋነትና ሀይማኖታችሁ በሚያዛችሁ መልኩ ስነስርዓት ይኑራችሁ
Dec 18, 2024በእውነቱ ከሆነ ሸጋ እይታ ነው እስኪ እኔ መናኛው ከማብራራልህ ይልቅ ይህንን ቪዲዮ ሳትሰለች በጥሞና አዳምጠው እና ምን እንደገበየህ ተመለስና ንገረኝ:: https://m.youtube.com/watch?v=3AakQxKl6N4&pp=ygUN4Yiu4YicIDjhjaEzNA%3D%3D
Dec 19, 2024