ሠላም ቤተሰብ, እንዴት ናችሁ ? ዛሬ አንድ ነገር ላካፍላችሁ እወዳለሁ። ምክንያቱም አሁን ላይ ከባድ የጭንቅ ግዜ ላይ ነኝ እናም ከናንተ ምክር ቢጤ እፈልጋለሁ ። እኔ እድሜዬ 26 ስሆን የምኖረውም አዲስ አበባ ነው። ተቀጥሬ የምሰራው አንድ ትልቅ ባንክ ውስጥ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማስተርስ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነኝ። አሁን ስለራሴ ማውራት ፈልገ አደለም። ያሳደገችኝ አክስቴ ናት። አባቴ ገና ህፃን እያለሁ/ነብሴ ሳያውቅ ነበር ያረፈው። እናቴም እደዛው ነብሴ ሳያውቅ ነበር ጥላኝ የጠፋችሁ። ምንም እንኳ አሁን ላይ አድጌ እናቴን ባገኛትም በውስጤ ትልቅ የ Identity/የማንነት ጥያቄ አለብኝ። ታዲያስ ይህ ነገር ከ ግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ከቶኛል። በራስ መተማመነ እየቀነሰ ብቸኝነት እየተሰማኝ ነው። TG-@abi000000
Dec 15, 2024የማንነት ጥያቄዎች ታዲያ በወላጅ ኮ አይመለሱም። እዚህ ምድር ላይ ግን እናትም አባትም ከሌለህ በትልቁ ትሰቃያለህ። እረዳሃለሁ ማለት አይደለም ግን ወላጅ ያላቸው ልጆችም በትልቅ ብቸኝነት ውስጥ አበሳቸውን እየበሉ ይኖራሉ።አታውቅ ይሆናል ግን እናት ኖሯቸው እናታቸውን የሚፈልጉ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጋ። ይህ ስሜት መምጣቱ ጥሩ ነው። ቢቀጥልም በመጥፎ አትውሰደው በህይወት ውስጥ አሳዛኝ ነገሮች የሚከሰቱት የአመታት ጥያቄም ሆነ ሀዘን ካለ ሊቋጭልህ ነው። መልስህን ዘገየም ፈጠነም ታገኘዋለህ። ጉዞውን በዚህ ስሜት ጀምረኸዋል። ልክ ሊነጋ ሲል ይጨልማል እንደሚባለው... በምን እንደምንረዳህ ባላውቅም ሰው በትክክለኛ መንገድ ካለበት ህመም መከራ ጎትተው የሚያወጡህ እነዚህ የብቸኝነት የድብርት የጭንቀት የበታችነት ስሜት መሰማት ኢንትሮቨርት መሆን ራስን የማጥፋት ስሜት የራስን የመጥላት ስሜት በሰዎች መከዳት መገፋት ማጣት ከሰራ ያለምንም ምክንያት መባረር ..ወዘተ.. ናቸው!!! አንተም ካለህ ጨምርበት እነዚህ ምድር ላይ የማይገኙ የእውነተኛው ድህነት የውስጥ ሰላም እና እረፍት መነሻ መቀስቀሻ ደውሎች ናቸው። እነሱ ራሳቸው ይመሩሃል። በተለይ ይህን ለተረዳ ሰው በነሱ ከመዋጥ ይልቅ ለምን ወደ ህይወቱ እንደመጡ ተገንዝቦ ከእስራቱ ነፃ ይወጣል እንዲሁ ህይወቱን ያስተካክላል። እንግዲህ መልስህን እንድታገኝ እመኛለሁ 😊🙏
Dec 16, 2024