ስላም! በጭንቀት በሽታ በጣም እየተስቃየሁ ነው እባካችሁ የምትረዱኝ ካላችሁ ወይም በነፃ መታከም የምችልበት መንገድ ካለ የምታውቁ ንገሩኝ #mental health
Dec 13, 2024ጤኔ ጣብያ የ ስነ አዕምሮ ህክምና ፈልጌ ነው ብለሽ መታከም ትችያለሽ ግን መንገር ያለብሽን ብቻ ተናገሪ እነሱም እንደኛ ሰዎች ናቸው
Dec 13, 2024ስላም! በጭንቀት በሽታ በጣም እየተስቃየሁ ነው እባካችሁ የምትረዱኝ ካላችሁ ወይም በነፃ መታከም የምችልበት መንገድ ካለ የምታውቁ ንገሩኝ #mental health
Dec 13, 2024ጤኔ ጣብያ የ ስነ አዕምሮ ህክምና ፈልጌ ነው ብለሽ መታከም ትችያለሽ ግን መንገር ያለብሽን ብቻ ተናገሪ እነሱም እንደኛ ሰዎች ናቸው
Dec 13, 2024ስላለፍኩበት እያለፍኩበትም ስለሆነ እረዳሻለው! ያገዙኝን አንዳንድ ነገሮች ላካፍልሽ ምናልባት ማውራት ከፈለግሽም user nameን አስቀምጥልሻለው! በነገራችን ላይ የጭንቀት መንስኤው ምልክቱም ሆነ አይነቱ ከሰው ሰው ይለያያል! ጭንቀትን ከባድ የሚያደርገው አውጥቶ ለሰው እንዲ ነው የሚሰማን ብሎ መናገር ከባድ መሆኑ ነው! ባለንበት ማህበረሰብም የግንዛቤ ችግር ስላለ ሰዎች ችግሩም አይረዱትም! ለምሳሌ እኔ ስለሚሰማኝ ነገር ስናገር ከተባልኩት መካከል “ምን ጎደለብህ፣ አትቅበጥ፣ ከመንፈሳዊ ህይወት ስለራቅክ ነው ....” እውነታው ግን ያ አይደለም! ብቻ ጭንቀትን ለመቋቋም ከሚያግዙ ነገሮች መካከል 1. ለሚያምኑት እና የቅርብ ለሆነ ሰው የሚሰማንን ስሜት መናገር! እገዛ እንደሚያስፈልገን በቁም ነገር ማዋየት 2. ልክ ጭንቀቱ ሲሰማን የፈጠረብንን ስሜት በዝርዝር በፅሁፍ ማስፈር! ስሜቱን የቀሰቀሰብንን ነገር (Trigger) የሚያደርገውን ነገር ለመለየት ያግዘናል! በቀጣይ ጊዜ ከእነዚህ ነገሮች ለመራቅ ጥረት ማድረግ 3. ሙዚቃ ማዳመጥ ለአንዳንድ ሰዎች Classical/ ለስለስ ያሉ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ ሊሆን ይችላል፣ ለሌሎች ደግሞ ያደጉበትን ጥሩ ስሜትና ትውስታ የሚፈጥርላቸውን ሙዚቃ ማድመጥ ሊሆን ይችላል! መዝሙር ማድመጥም መንፈስን የማረጋጋት አቅም አለው። 4. ወደ መንፈሳዊ ህይወት ማተኮርም ጥቅም አለው! ስለ ፈጣሪ መልካምነት እና በአምሳሉ ለፈጠራቸው ፍጥረታት ምን ያህል እንደሚያስብ ማስተዋል የአመለካከት አድማስን ያሰፋል! 5. ብዙ ጊዜ የማናስተውለው ግን ጥሩ እንዲሰማን ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ መስጠት ነው! ብድር ሊመልሱልን ለማይችሉ፣ ቀን ዝቅ ላደረጋቸው፣ ፈጣሪን ተስፋ አድርገው ለሚኖሩ ምስኪኖች በስውርም ይሁን በይፋ መልካም ማድረግ! እንዳው የገንዘብ አቅም እንኳ ባይኖር እናቅርባቸው፣ ሰሚ ጆሮ እንስጣቸው፣ አብረናቸው እንብላ ይህ በራሱ ስሜት ላይ ብዙ ለውጥ ያመጣል! 6. አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይህ ሲባል የግድ Gym መግባት ያስፈልጋል ማለት አይደለም! ቤት ውስጥ የሚሰሩ ቀላል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ አሊያም ምሽት ላይ የእግር መንገድ መጓዝ (walk) ማድረግ ጠቃሚ ነው! 7. አንዳንዴ ጭንቀት የሚሰማን ማድረግ የምንፈልጋቸውን ነገሮች እንዳናደርግ ሀይላችንን እንደተነጠቅን ስለሚሰማን ነው! ስለዚህ ይህን ሃይላችንን ለማስመለስ ትንሽም ቢሆን የቤት ውስጥ ስራ መስራት ትልቅ ለውጥ ያመጣል! አልጋ ማንጠፍ፣ የተወሰኑ ልብሶችን ማጠብ፣ ምግብ ማብሰል ... 8. ጭንቀቱ እየባሰ እየመጣ እንደሆነ ከተሰማ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ጥረት ማድረግ! አውቃለው ሲያወሩትና ሲኖሩት ቀላል አይደለም! በአንድ ውጊያ ድል የሚነሳበት ጦርነት አይደለም፤ የራስ ጠላት ራስ እንደሆነ ነው የሚሰማው! ከ10 ዓመታት በላይ የኖርኩበት ስለሆነ ስሜቱ ይገባኛል! ግን ደግሞ የጨለማ ቀናት እንዳሉ ሁሉ ብርሃን የሚወጣባቸው ውብ ቀናትም ይኖራሉ! ሁሌም ለራሴ የምደግመው አባባል “ይህም ያልፋል” የሚለውን ነው! የማይነጋ ሌሊት የለም ትንሽ ትዕግስት፣ ትንሽ ተስፋ እና ትንሽ እምነት ብዙ ለውጥ ታመጣለች! ብዙ አወራሁ ከብዙ ጥቂቱ ከጠቀመ እሰየው! መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ ... @Mahershallalhashbaz
Dec 13, 2024አመስግናለሁ
Dec 13, 2024Meditation jemere kecalsh merte mibalu course awredesh kenesu eyayesh mejemer ticiyalesh beatam effective nw
Dec 13, 2024username askemcui be wst. If you're student sew agenagnshalew
Dec 13, 2024ከቻልሽ ለ ሳምንት ወይ ለአስራ አምስት ቀን ሱባኤ ግቢ እና ደሞ ሲጨንቅሽ ሲጨንቅሽ መዝሙረ ዳዊት ጸልዪ እግዚአብሔር ይርዳሽ
Dec 14, 2024እሽ! አሜን
Dec 14, 2024ካገዘሽ ይሄን Ai ሞክሪው
Dec 13, 2024እሽ እሞክረዋለሁ
Dec 13, 2024ምንድነው ሚያስጨንቅሽ?
Dec 13, 2024