Selam guys and tyake alegn pls, ene 19ameten ahun lyez new behiwote abzagnawn gizeyen yatefahut addadis negrochn bemear ena technlogy lay beabzagnaw yeneberew , ena i feel like belelaw negeroche(social life, friends, church life❤) ena guys wedehulal yekerew ymeslachuhal lenegeroch weyns ..pls temokroachun ngerugn ena mkrachun thanks yemr🙏
Dec 12, 2024ሰላም! ይሄ ስሜት እውነቱን ለመናገር አብዛኞቻችን የምንጋራው ስሜት ይመስለኛል፤ ማለትም በህይወታችን መድረስ አለብን ብለን የምንመኘው ቦታ ጋር ለመድረስ ስንል ነገሮችን መስዋዕት ስናደርግ እንስተዋላለን። ደስ የሚለው ግን ጥሩ ዕድሜ ላይ ነው የነቃኸው/ሽው። ሰዎች ስንባል ትልቁ ስህተታችን የማናውቀውን ነጋችንን በእኛ ቁጥጥር ስር ማድረግ ስለምንፈልግ ውድ ስጦታ የሆነው ዛሬያችንን ሳንኖረው ያመልጠናል። መፍትሔው አንድ እና አንድ ብቻ ይመስለኛል! ዛሬ የሚባለው ነገር እስካለ ድረስ ይቆጩን የነበሩ፣ ሳናደርጋቸው የቀረናቸው አሊያም ልንሞክራቸው የምንፈልጋቸውን ነገሮች ዛሬ ላይ መኖር! ከተጠቀሰው ዕድሜ አንፃር አሁንም አልረፈደም! ይህን ስል ግድ የለሽ የሆነና ራስንም ሆነ ህልምን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ውስጥ for the sake of fun መግባት አለብን እያልኩ አይደለም! ግን ጤናማ ግንኙነት፣ ጤናማ አስተሳሰብ እና ጤናማ ማንነትን ለመገንባት አንዳንድ ጊዜ ከcomfort zone ወጣ ብሎ ነገሮችን መሞከር ጥሩ ይመስለኛል።
Dec 12, 2024