ሰላም ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ? ይህንን ጥያቄ የማቀርበው ለፕሮቴስታንቶች ነው። ትልቁ ኦርቶዶክስ እንዳትሆኑ የሚያደርጋችሁ/መልስ የለውም የምትሉት ምክንያታችሁ/ጥያቄያችሁ ምንድን ነው?😊 Let me know👇👇👇
Dec 11, 2024ጥሩ ስለዚህ ምክንያቶቹ እነዚህ ናቸው። 1. ወንጌላዊያን ጽድቅ በእምነት ብቻ እንደሆነና አስተምህሮውም የቤተክርስቲያንን ህልውና የሚወስን ነው ብለው ያምናሉ። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ጽድቅ በእምነት ብቻ ሳይሆን በመልካም ስራም ይጸደቃል ብለው ያምናሉ። 2. ወንጌላዊያን ደኅንነት በጸጋው ብቻ ነው ብሎ ያምናሉ። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ደኅንነት በጸጋ ብቻ ሳይሆን በሰዎች መልካም ስራ ጭምር ነው ብለው ያምናሉ። 3. ወንጌላዊያን በቅዱሳት መጸሃፍት የበላይና የመጨረሻ ባለስልጣንነት መርህ ያምናሉ። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን መጸሃፍ ቅዱስን በብቸኝነት መሳሳት አለመቻልና የበላይ ስልጣን መሆን አያምኑም። ይልቁኑ ከመፅሐፍቅዱሱ እኩል ስልጣን ያላት ልትሳሳት በማትችል ቤተክርስቲያን ያምናሉ። 4. ወንጌላዊያንና በ66ቱ ብቻ የቅዱሳት መጸሃፍት ቀኖና ይመራሉ ፤ እርሱንም ብቻ የአምላክ እስትንፋስ አድርገው ይቀበላሉ። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን በየትኛውም ትውፊት ፈፅሞ የማይታወቀውን 81 የሆኑ የቅዱሳት መጸሃፍትን ቀኖና ይቀበላሉ። 5. ወንጌላዊያንና ሉተራዊያን በ Ecclesiological Exclusivism አያምኑም። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ከኛ በረት ውጪ ላሉት በጎች የመዳን መንገድ የላቸውም ብለው ያምናሉ። 6. ወንጌላዊያን ወደ ሞቱ ቅዱሳን መጸለይ ፣ መዘመር ፣ በስማቸው ታቦት አሰርቶ መስገድን ከጣኦት አምልኮ ለይቶ አያዩም። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ሞቱ ቅዱሳን መጸለይ ፣ መዘመር ፣ በስማቸው ታቦት አሰርቶ መስገድን የአምልኮአቸው ዋናው ማእከል አድርገው ያምናሉ። 7. ወንጌላዊያን ስእል ሰርቶ በፊቱ መስገድ ፣ ስእሉ እንዲረዳቸው ወደ ስእሉ መጸለይ ፣ በስእሉ በኩል ለአምላክ ጸሎት ፣ ቅዳሴ ፣ ምስጋና ማቅረብ ይጠየፋሉ። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ስእል ሰርቶ በፊቱ መስገድ ፣ ስእሉ እንዲረዳቸው ወደ ስእሉ መጸለይ ፣ በስእሉ በኩል ቅዳሴ ፣ ምስጋና ፣ ለአንዱ አምላክ እጣን ማጠን የአምልኮአቸው መካከለኛ አስተምህሮ ነው። 8. ወንጌላዊያን ማርያም እንደማንኛውም ሰው እንደሞተች ፣ ወደፊትም እንደሌሎቹ በትንሳኤ ዘጉባኤ ካረፈችበት ትነሳለች ብለው ያምናሉ። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ማርያም አስቀድማ ከሙታን መካከል የተነሳች ፣ ስጋዋም ከመበስበስ ተጠብቆ ትንሳኤ ሆኖላት ወደ ሰማይ እንደተወሰደች ያምናሉ። 9. ወንጌላዊያን ቅድስት ማርያም የአዳም የሃጢአት ውርስ እንደነበራት ፣ በልጇ ደም እንደሌሎች ሰዎች ሁሉ እንደነጻች ያምናሉ። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ማርያም የአዳም የውርስ ሃጢአት የለባትም ብለው ያምናሉ። 10. ወንጌላዊያንና በነገረ ክርስቶስ አንድ አካል ሁለት ባህርይ ብለው ኬልቄዶናዊ የነገረ ክርስቶስ አስተምህሮ ያምናሉ። ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ከሃዋሪያዊ የነገረ ክርስቶስ አንድ አካል ሁለት ባህርይ ከሚለው አስተምህሮ የተቆረጡ ናቸው። 11 ወንጌላዊያን ማርያም ከሌሎች ፍጡራን የተለየች፣ በሰማይ በእግዚአብሄር ቀኝ የቆመች የሰማይና የምድር ንግስት፣ አስታራቂ አማላጅ፣ የምህረት ኪዳን የተገባላት የሚል አስተምህሮ ሰው ሰራሽ፣ አጋንንታዊ ጠያፍ ትምህርት እንደሆነ ያምናሉ፤ ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ማርያም ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች፣ የሰማይና የምድር ንግስት፣ በእግዚአብሄር ቀኝ ቆማ ሰዎችን የምታማልድ፣ የምህረት ኪዳን ከልጇ የተቀበለች ናት ብለው ያምናሉ። 12 ወንጌላዊያን ክብርና ስግደት ለ እግዚአብሄር ብቻ እንደሆነ ያምናሉ፤ ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊያን ክብርና ስግደት ለእግዚአብሄር፣ ለማርያም፣ ለመላእክት፣ ለጻድቃን ለሰማእታት፣ ለመስቀሉ፣ ለታቦት፣ ለተቀደሱ ስፍራዎች፣ ለቤተመቅደስ እቃዎች ሁሉ ይገባል ብለው ያምናሉ። እንዲህ እያልን ብዙ ነጥቦችን ማንሳት ይቻላል። ይህን በጥሩ ልቡና ላነበበ አንባቢ በቂ መልስ ይመስለናል!
Dec 11, 2024