ወንድ ልጅ ከሶስት አራት ሴቶች ጋር ሲታይ ዝም ይባላል ወይም ብዙም ትኩረት አይሰጠውም። ለምንድን ነው ሴቶች ከሶስት ወንድ ጋር ስትታይ እንደ ወሲብ እንደምትፈፅምና እንደ ባለጌ የምትታየው ? ለምን ወንዶች ላይ ትኩረት ሳንሰጥ ለምን ሴቶች ላይ ? ለወንዶች ትኩረት ባለመስጠታችን ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ማንኛውንም ድርጊት በተዘዋዋሪ እየደገፍን አይደለም ወይ !? ሀሳብ ካላችሁ ብታካፍሉን! ሀሳባቹህን ለመግለፅ አማርኛ ፣ English መጠቀም ትችላላቹህ።
Dec 03, 2024በትክክል። ወንዶች ከብዙ ሴቶች ጋር መሆን እንደ ጀግንነት እየታየ ነው። በአንጻሩ ሴቶች ከብዙ ወንዶች ጋር ከታዩ ደግሞ እንደ ባለጌ ነው የሚታዩት። ይሄ መቆም አለበት። ሴትም ወንድም አንድ ለአንድ ነው መኖን ያለባቸው።
Dec 03, 2024