Please wfret betam aschegeregn 20 amete nw ena BMI 27.6 dershalehu chirash lemekenes bemokerku kutr eyechemerku nw ena yalegnin confidence betam eyatahu nw lbs mrcha eyetechegerku nw sew laggnish silegn des aylegnim cos sngenagn yemejemeria asteyayetachew wefersh yemilew nw ena bezih guday sewnetachihun yastekakelachihu lmd yalachihu sewoch ebakachihu erdugn
Dec 03, 20241. ስለሰዎች አመለካከት ሳይሆን ስለ ጤንነት አስቢ። 2. ውፍረት እንደ አመጣጡ ነው የሚሄደው በአምት ዓመት ወፍረሽ በአምስት ወር አትከሺም። የዛሬ አምስት ዓመት የነበርሽበት ክብደት ጋር ለመድረስ አምስት ዓመት ይፈጅብሻል እያልኩ ሳይሆን ሰውነት ጊዜ ይፈልጋል adjust እያደረገ ነው የሚቀንሰው። 3. በምናምን ሻይ በምናምን ቅጠል ወይም በምናም ታብሌት እያልሽ ለመቀነስ አትሞክሪ። ውጤታማነታቸው አነስተኛ ነው ውጤታማ ቢሆኑ እንኳን ጤናማ አይደሉም። በአካል ብቃት እንቅስቃሴና በአመጋገብ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመቀነስ ሞክሪ። 4. አመጋገብሽን አስተካክዪ። ካርቦሃይድሬትና ቅባት (fat) ይዘት ያላቸውን ምግቦች ቀንሰሽ አትክልትና ፕሮቲን ይዘት ያላቸውን ምግቦች በብዛት ተመገቢ። 5. ክብደት መቀነስ ፕሮጀክት ነው ከዕቅድ ጀምሮ እስከ አፈፃፀም የሚሄድ። በአቋራጭ ብትደርሺበት እንኳን ውጤቱ ዘላቂ ስለማይሆን የፕሮጀክቱን ሂደት በአግባቡ መከተል አለብሽ። ቁርጠኝነት (commitment) ይፈልጋል። 6. ሳይንሳዊ የሆኑ የተጠኑ አመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አጣምረው የያዙ እንደ Intermittent fasting ያሉ መንገዶችን ተከተይ።
Dec 03, 2024