ሁሌ ግራ ሚገናኝ ነገር ነው እና እባካችሁ መልሱልኝ ግልፅ አድርጋችሁ ፡፡ አንድ ሰው አላማውን እንዴት ሊያገኝ ይችላል ?? ማለትም ስለፈጠሪ ማያውቅ ፤ ግራ የገባው ግን መኖር የሚፈልግ ምን ማድረግ እንዳለበት ከየት መጀመር እንዳለበት ማያውቅ፡፡ የሚኖርለትን አላማ እንዴት ይወቀው፤ ስጋዊ ስሜቱን እንዴት ያሸንፈው ?? እኔ ሚገርመኝ እስካሁን እድሜዬ የኖርኩት በዘፈቀደ መሆኑ የገባኝ መኖር ልጀመር ብዬ ሳስብ ነው፤ሚገርመኝ ደግሞ አስተዳደጌም ይሄንን ሁሉ ነጥቆኛል ብዙ አጣው፤ብዙ ተጎዳው ግን አሁንም አይገባኝም እድሜዬ 27 ነው ከአንድ ወር ቡሃላ ደግሞ 28ኛዬን ይዛለው ፡፡ ብቻ አላማዬን እንዴት ላግኝ ወደ አላማዬ እንዴት ልጓዝ ትግሌን ስጀምር እንዴት ልጀምር አላውቅም ብቻ እስቲ ትንሽ አውሩኝ ፡፡ መርዳት ሚፈልግ ካለ ደግሞ በውስጥ አውሩኝ እባካችሁ 🙏🙏
Nov 22, 2024ለመነሻነት እንዲረዳህ ከቤተሰብ ጋር ምትኖር ከሆነ ግዜ ሳታጠፋ ውጣ የቆርቆሮ ቤትም ቢሆን በአቅምህ ተከራይና ኑሮን በግልህ ጀምር ... ራስህን ችለህ እየኖርክ ከሆነ ደግሞ ቀጣዩ ስቴፕ የትዳር አጋር ልትሆን ምትችለውን ፈጣሪህን እንዲሰጥህ ለምነው ብዙ ነገሮችህን ያቀልልሀል ይሄኛው እርምጃህ ደግሞ:: ትዳር ውስጥ ካለህ ደግሞ ልጅ ውለድ ይሄኛው ደግሞ ላንተ መኖርህን አቁመህ ለልጅህ ብቻ እንድትኖር መንገዱን ያበራልሀል... ለሁሉም ነግር ግን ዋንኛውፒላር(ምሰሶው) ሀይማኖትህን እወቅ ቀንም ማታም ፀልይ አመስግን ለብዙዎቻችን ዳገት ሚመስለን ግን ብዙ ሰዎች ደግሞ ተግብረውት ብዙ የተለወጡበት ሚስጥር ወደፈጣሪ መቅረብ ነው ... ስጋህን ጥለህ እንደምትሄድ ማሰብ አለብህ ነገር ግን ይሄ ስጋህ የተቀደሰ መሆኑን ባለመዘንጋት ነው ታዲያ ስጋህን አክብረው ነገርግን አትገዛለት
Nov 25, 2024