Endet nachw...teyakew le orthodoxawyan new Yemtkorb set mn aynet anuanuar new linorat yemigebaw?specifically sle alebabesua tsegur ye yeken lemdochua lihonu selemigebachew ngerugn please beteley yezih aynet nuro yemtnoru ehtoche endezih negn blo sle ras menager bikebdm le ehtachw asredugn hywetachhun...wendmochm hasab btsetugn ekebelalew🙏🙏
Nov 17, 2024ኦርቶዶክሳዊያን ልብ ልንለው እና ምን ጊዜም ልንዘነጋው የሚገባው ነገር ኹላችንም እንደቆረብን ነው ! ሥጋችን ከሥጋው ደማችን ከደሙ ተዋህዷል ! ! ስለዚኽ ቆራብያን ቅድመ ቁርባን ጊዜ ቁርባን እና ድኅረ ቁርባን ሊያደርጉ ከሚገባው ጥንቃቄ በተለየ እንደ ክርስቲያን የተለየ ሕይወት ሊኖራቸው አይችልም። አንድ ክርስቲያን ሊኖር እንደሚገባው ቆራብያኑ በተመሳሳይ መልኩ ይኖራሉ ! ቆራብያኑም አንድ ክርስቲያን ሊኖር እንደሚገባው እንዲኹ መኖር አለባቸው ! ክርስቲያን እንዴት ይኖራል ለሚለው ኹሉ በአግባብ እና በሥርዓት ይኹን እንዳለ አንድ ክርስቲያን ለአለባበሱ ለአረማመዱ ለአመጋገቡ ለአነጋገሩ በጥቅሉ ለተግባራቱ ኹሉ ሥርዓት የተሠራለት ነው። እለት እለትም አምላኩን ክርስቶስን ለመምሰል የሚጥር መኾን ይገባዋል ። ለሴትም ለወንድም ተወስኖ የተሠራ ሥርዓት እንደመኖሩ በዛ መሰረት ለመኖር ራስን ማለማመድ ነው ዋናው ነገር።
Nov 18, 2024