Atheist here ኦርቶዶክሳውያን ወንድም እህቶች፣ ብዙ ምእመኖችን እመለከታቸዋለሁ እና ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲህ የምትወዷት ለምንድን ነው? የሃይማኖቱ ተከታይ ብቻ ስለሆናችሁ አይመስለኝም፣ በትዕቢት አይደለም ግን እንዲው ለማወቅ ነው?
Nov 04, 2024ጣዕሟን እንዴት ብዬ ልንገርህ ሳትቀርባት ሳትረዳት ማለት ከየቱ ልጀምርልህ እንኳን እንዲሁ ሩቅ ሆነህ ቀርበሀትም እሷን መግለፅ አይቻልም 🕯ቸር አምላክ ፍቅሯን በልቦናህ ጣዕሟን በከንፈርህ ይጻፍልህ 🙏🙏 ስለ ትህትናዋ ልንገርህ?? ስለ ድንግልዋ ልንገርህ?? ስለ ርህራሄዋ ልንገርህ?? ስለ እርጋታዋ ልንገርህ?? ከየት ብዬ ልጀምርልህ ይልቅ ቅዱሳን አባቶቼ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ስለ እርሷ ያሉትን ጥቂቷን ላካፍልህ 👇👇 🕯...ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች እድፍ የምታውቂ አይደለሽም በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ ....እግዚአብሔር አብ ንጽሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ መልአኩን ወደ አንቺ ላከ፣ መንፈስ ቅዱስ በላይሽ ይመጣል፤ የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል አለሽ 🕯...እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሆኖ ምስራቅንና ምዕራብን ሰሜን እና ደቡብን ዳርቻዎችንም ሁሉ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰ አሻተተም እንደ አንቺ ያለ አላገኘም የአንቺን መአዛ ወደደ ደም ግባትሽንም ወደደ 🕯...የሚወደውን ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ። ድንግል ሆይ በምን እና በምን ቃል አንቺን መግለጥ ይቻለናል
Nov 04, 2024