ሰላም ሰዎች እነዚህን ጥያቄዎች ተባበሩኝ ኦርቶዶክስ የሆናቹ ብቻ! 1,ሮብ እና አርብ ጾምን ያስጀመሩት አባት ማን ናቸው? 2,በትውፊት የተወረሱ ስርዓቶች ውስጥ አምስቱን 3, በጸሎት ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባን የሚነግረን የፍትሀ ነገስት አንቀጽ ስንት ነው? ምንስ ይላል?🙏🙏
Oct 25, 2024🚩 እሮብ፥ አርብ? በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች እምነት መግለጫ የነበረ ዲዳኬ (Didache) የተባለ መጽሐፍ አለ። "ዲዳኬ" የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን አስተምህሮ ወይንም ትምህርት ማለት ነው። የመጽሐፉ ሙሉ ስም "The Teaching of The Lord through his twelve apostles to the nations" ወይንም "የጌታ ትምህርት በሐዋርያቱ በኩል ለዓለም" የተሰኘ ነው ይህ መጽሐፍ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የተጻፈ መጽሐፍ እንደሆነ ሁሉም የዘርፉ ምሁራን ይስማማሉ። ወይ በሐዋርያት በራሳቸው ወይንም ደግሞ በእነርሱ ቀጥተኛ ተማሪዎች እንደተጻፈ ይታመናል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ፥ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እምነት፥ አኗኗር፥ ቅኖና፥ የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮች በሙሉ ተዘርዝረው ተቀምጠዋል። 🚩 ይህ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ምን ብለው እንደሚያምኑና፥ እንዴት ይኖሩ እንደነበር ያሳውቀናል። ዛሬ እስቲ አንድ አስገራሚና ለአሁኑም ዘመን ይጠቅመናል ያልነውን አንድ ልምምዳቸውን እንመልከት፦ But let not your #fasts be with the hypocrites; Mathew 6:16 for they #fast on the second and the fifth day of the week; but #fast on the #fourth day and the preparation (#Friday). [ Chapter 8, Concerning Fasting and Prayer (the Lord's Prayer) ] ከላይ እንደምትመለከቱት፥ ጾምና ጸሎትን በተመለከተ የሚናገረው ነገር አለ። ማቴ 6:16 ከጠቀሰ በኋላ ጾም እንደ ግብዞች እንዳይሆን ያዝዛል። ከዚያም ክርስቲያኖች ከዚህ በተቃራኒ በአራተኛው ቀን (ረቡዕ) እና በዝግጅት ቀን (በአርብ ቀን) እንዲጾሙ ያዝዛል። 🚩 ይህ ማለት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እሮብና አርብን ይጾሙ ነበር ማለት ነው! እሮብና አርብን መጾም ከሐዋርያት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ክርስቲያናዊ ልምምድ ነው። ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የሆነ ተጨባጭ ማስረጃ አለና። በሆነ ሰዓት ላይ የተፈጠረ ስርዓት ሳይሆን፥ የሐዋሪያትና የቀደሙ ተከታዮቻቸው ስርዓት ነው። አርብ የዝግጅት ቀን የተባለው፥ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነ፥ ለሰንበት ይዘጋጁ የነበረው አርብ ነበር። በዚያም ምክንያት የዝግጅት ቀን ተባለ። የሳምንት መጀመሪያም እሁድ ቀን ስለሆነ፥ አራተኛው ቀን ረቡዕ ነው ስለዚህ ስለ ጾም ይህን አውቀን የሐዋርያትን እና የመጀመሪያዎቹን ክርስቲያኖች መንገድና ሕይወት እንከተል! 🚩 አጠር ያለ መጽሐፍ ነው፥ በቀጥታ ማንበብ ለምትፈልጉ ሊንኩ ይኸው👇 https://www.newadvent.org/fathers/0714.htm ይህንን ካነበቡ ቦቱ ስለማይችል ኑ ወደ አፖስቶሊክ ዲስከሽን
Oct 25, 2024