ሱስ በጣም ከባድ ነገር ነው። ስለመከርሽው..አታድርግ ማለት እንኳ እንደ አድርግ ይቆጠራል። እኔም እንዳንቺ ወንድም አለኝ ከባድ ሱስ አለበት.. ድሮ ድሮ ብዙ ነገር ለማድረግ እሞክር ነበር እንዲህ እንዳንቺ..በመጨረሻ የማይሆን ነገር ውስጥ ሲገባ ማገገሚያ እንዲገባ ለማድረግ ከቤተሰብ ጋር ሳወራ ልጃቸውን የምገልባቸው መስሏቸው እኔን አገለሉኝ። የእሱም የቤተሰቤም የኔም ህይወት እየተበላሸ ሲመጣ እሱን ለማዳን ስሞክር እኔ ልገደል እንደሆነ ሲገባኝ ከቤተሰብ ርቄ መኖር ጀመርኩ..እስካሁን በህይወት አልቆይም ነበር። እሱም ማገገሚያ መግባት አለበት የሚለው ወሬ እኔ እንዳወራሁ ሲያውቅ ሊገድለኝ ያሳድደኝ ነበር ተመልከቺ አሞት እንጂ ስቃዩ ከብዶበት ለራሱ እስከማያስብ ድረስ የሚያስብለትን ቤተሰብ የሚያጠፋ የሚያህል ሰይጣን ተሸክሞ እየዞረ እሱን መምከር መቆጣት ከባድ ነው። አንዳንዴም ነገሮችን በራሳቸው እንዲስተካከሉ መተው እና ራስን ማዳን ጥሩ ነው። አሁን ላይ ግን እሱም ወደ ራሱ እየተመለሰ ነው። ሱስ አለብኝ ማገገሚያ መግባትም እፈልጋለሁ እያለን በራሱም ለመተው በመጣር ላይ ነው። አውራልን ሳንለው የሚያወራልን ብዙ ለአመታት የደበቃቸውን አጋጣሚዎች ነው። አንድ የሲጋራ ወይም የመጠጥ ሱሰኛን ያ ነገር እንደማይሆነው እንደሚገድለው እያወቅሽ ተው ከምትዪው እንካ አጭስ እንካ ጠጣ ብትዪው የሚያረገውን ነገር ማስተዋል ይጀምራል። ምንም እንዳፈሪ በምድር አንቺ ሰዎችን ጠበቅሻቸውም አልጠበቅሻቸውም የሚሆነው ነገር ከመሆን አይቀርም። እኔ የምልሽ ነገር ስለራስሽ ህይወት አስቢ..በመሃል አትጎጂ..ራስሽን ማዳን ስትቺዪ ሌሎችም ይድናሉ ..!! ለእኔ በወንድሜ ዙሪያ ላየሁት ለውጥ አመስጋኝ ነኝ። ነገሮችን ስትተያቸው መስተካከል ይጀምራሉ .. ራስሽን ጠብቂ
Oct 19, 2024