ሰላም ቤተሰቦች የethio telecom share (አክሲዮን) አሁን ላይ ብንገዛ ከ2 or ከ3አመታት በዋላ ዋጋው አሪፍ ሊሆን ይችላል እናም ትርፉ አሪፍ ሊሆን ይችላል??
Oct 19, 2024✍🏽 የገቢና የትርፍ (Revenue& Earning)ልኬት ነው። ቢያንሰ ባለፉት አምስት አመታት የድርጅቱ ገቢ ምን ያክል ነበር? በምን ያህል እያደገ ነው? የትርፉ ምጣኔስ? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ማስላትና ሂደቱን መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ የኢትዬ ቴሌኮምን የገቢና ትርፍ እድገት ስንመለከት በ 2020 ገቢው 56 ቢሊየን ብር አካባቢ የነበረ ሲሆን በሰኔ 2024 ደግሞ 93•7 ቢሊየን ብር ደርሷል። ይህ በአማካይ የገቢው እድገት 21% አካባቢ እንደሆነ ያሳያል። ✍🏽ሌላው የፋይናንሰ ጤንነት መለኪያ የሼር ገቢ (Earning per share)ነው። በዚ ቀመር የድርጅቱ አንድ ሼር በአመቱ ምን ያክል የትርፍ ምጣኔ አገኘ የሚለው ይሰላል። ለምሳሌ: ኢትዬ ቴሌ ኮም ባለፈው የሂሳብ አመት የተጣራ ትርፉ 21•79 ቢሊየን ብር እንደሆነ ተገልጽዋል። ይህ ትርፍ ድርጅቱ ላለው አጠቃላይ የሼር ብዛት (1 ቢሊየን) ሲካፈል 21•79 ብር የሼር ገቢ ምጣኔ ይኖረዋል። ይህም ማለት አንድ ሼር 21•79 ብር ትርፍ ይኖረዋል። አሁን ባለው የሼር ዋጋ አንዱ ሼር 300 ብር የሚሸጥ በመሆኑ የ 300 ብር ኢንቨሰትመንት በአመት 22 ብር አካባቢ ትርፍ ያሰገኛል። ይህ ትርፍ ያለፉት አመታት እድገቱን ከተከተለ በየአመቱ በአማካይ 21 ፐርሰንት እያደገ ይሄዳል። ✍🏽ሌላኛውና ወሳኝ የሚባለው የፋይናንሰ መለኪያ PEG ratio ይባላል። የአንድ ሼርን ትርፍ እድገትን ግምት ውስጥ አሰገብተን የምናሰላበትና የሼሩ ዋጋ ተገቢ ነው? በዝቶበታል? ወይንስ ርካሸ ነው የሚል የሚያመላክተን ነው። የቴሌን ምሳሌ ቀጠለን ብንመለከተው የአንድ ሼር ትርፍ 22 ብር አካባቢ እንደሆነ አይተናል። ይህን የአንድ ሼር ትርፍ ለአመታዊ እድገቱ ማለትም 21 ፐርሰንት (በሙሉ ቁጥር) ሰናካፍለው 1•04 አካባቢ ይመጣል። የአንድ ሼር PEG ratio ከ1 በላይ ከሆነ የሼር መሸጫ ዋጋው ውድ መሆኑን ያመላክታል። ✍🏽ከነዚህ በተጨማሪ ለውሳኔ የሚያግዙን ንፅፅራዊ የሆኑ የፋይናንሰ ጤንነት መለኪያዎች አሉ። ከነዚህ ቀዳሚው የሼር ትርፍ ንጻሬን(EPS ratio) ከሌሎች ትርፎች ጋር ማነጻጸር ነው። ከላይ እንዳየነው የኢትዬ ቴሌኮም የአንድ ሼር ትርፍ 22 ብር አካባቢ ነበር። ይህን ትርፍ በአንድ ሼር መሽጫ ዋጋ ስናካፍለው (22/300)= 7 ፐርሰንት አካባቢ ነው። ሰለዚህም ባለፈው የሂሳብ አመት የቴሌ ሼር የትርፍ ምጣኔ 7 % ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ ከባንክ የቁጠባ ወለድ በታች ከመሆኑ በተጨማሪም ከሌሎች ኢንቨሰትመንቶች የትርፍ ምጣኔ ያነስ ነው። ✍🏽 ግምት ውስጥ መግባት ካለበት የአይነታዊ መለኪያ አንዱ የድርጅቱ የቢዝነሰ ሞዴል የእድገት ተስፋ ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ከቴሌኮም ሰርቪስ በተጨማሪ ግዙፉ የዲጂታል ፋይናንሰ(Fin-Tech) ተቋም እየሆነ መጥቷል። ይህም የድርጅቱን እድገት ብሩህ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዬ ቴሌኮም ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ያፈሰሰ በመሆኑ ባለፉት አመታት ትርፉ ያነስ የመሆን እድሉና ወደፊት የማደግ ተሰፋ እንዳለው አመላካች ነው። ✍️የአንድ ድርጅትን ሼር ለመግዛት እነዚህ መለኪያዎች በቂ አይደሉም። ወሳኙ መለኪያ መግዛት የፈለግንበት ምክኒያት ነው። ከትርፍ ባሻገር ባለቤት የመሆን፥ ተጽዕኖ የመፍጠር፥ ውርስ የመሳሰሉ ምክኒያቶች ሊኖሩን ይችላሉ። ሌላው እጃችን ላይ ያለው የገንዘብ መጠንና ያሉን አማራጭ ኢንቨሰትመንቶች ውሳኔያችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ።» «የኢትዬ ቴሌኮም የሼር ሽያጭን በተመለከተ ለውሳኔ የሚያግዙ የፋያናንሰ ጤንነት መለኪያዎችን በተመለከተ አንድ ልጥፍ አቅርቤ ነበር። ሆኖም የተወሰኑ ግልፅ አልሆነልንም የሚል ጥያቄዎች ደርሰውኛል። በቀላል ነጥብ ለማሰረዳት ልሞክር። ለሽያጭ የቀረበው ሼር የአንዱ መግዢያ ዋጋ 300 ብር ነው። በተጨማሪ 1•5 ፐርሰንት ሰርቪስ ቻርጅና ከሰርቪሰ ቻርጁ ላይ የሚሰላ ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ አለው። አንድ ስው 1000 ሼር መግዛት ቢፈልግ 👉 የሼር ክፍያ 300 ሺ ብር 👉 ሰርቪሰ ቻርጅ 4500 ብር 👉 የተጨማሪ እሴት ታክሰ 675 ብር በድምሩ 305,175 ብር ይከፍላል። ይህን ሼር የሚገዛው ለትርፍ ከሆነ፥ በዚህ ብር ምን ያክል አተርፋለሁ የሚለው ዋነኛ ጥያቄ ይሆናል። መልሱን ለማግኘት መጀመሪያ ኢትዬ ቴሌኮም ባለፈው አመት ሰንት አተረፈ እና የትርፍ እድገቱስ ስንት ፐርሰንት ነው የሚለውን ማወቅ ያሰፈልጋል። በዚህ መሰረት የኢትዬ ቴሌኮም ያለፈው አመት 👉 የአንድ ሼር ትርፍ 22 ብር አካባቢ ነበር። 👉ያለፉት አመታት አማካይ የትርፍ እድገት 21 ፐርሰንት አካባቢ የነበረ ሲሆን እድገቱ በዚሁ ከቀጠለ የዚህ አመት የአንድ ሼር ትርፍ 27 ብር አካባቢ ይሆናል። 👉 ይህም አንድ በ300 ብር የተገዛ ሼር 27 ብር አካባቢ ያተርፋል ማለት ነው። 1 ሺ ሼሮችን 305 ሺ ብር አካባቢ አውጥቶ የገዛው ሰው ትርፉ 27 ሺ ብር ይሆናል። ይሄን መግዛት ያዋጣኛል አያዋጣኝም ግላዊ ውሳኔ ነው።» ©: Ibrahim Abdu
Oct 19, 2024