ስለ ምእላድ ዘር እና "ንባቡ ከየማን ፍቺው ከአሚን " የሚለውን part ብጥር አርጋቹ አስረዱኝ "የማን" ማለት ቆይ is it as in "whose"?
Oct 04, 2024ምዕላድ ከግስ መጨረሻ ላይ ባዕድ በመጨመር የሚወጣ ነው። ንባቡ ከየማን ያለሽ በጥሬው በገጸ ንባቡ "ሃይማኖት" በቀኝ የሚያቆም ነውና ። የማን ማለት ቀኝ ነው። ቀኝ አለ ቀኝ የክብር ስፍራ ነው። አንድም ቀኝ ኃይልን የተላበሰ ነው ። አንድም ቀኝ ቢወድቁ የሚነሱበት ነው። አንድም ቀኝ የራቀውን የሚያቀርቡበት ነው። ወደ የማናዊ ግብር የሚመራ ነው አለሽ የማናዊ ግብር ንስሐ ነው። ( በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ ፈያታዊ ዘየማን እንዳለው ፈያታዊ ዘየማን ወንበዴ ነበረ በመስቀል ላይ ሳለ ወንበዴነቱን አምኖ ኢየሱስንም " ጌታ ኾይ በመንግስትኽ በመጣኽ ጊዜ አስበኝ " እንዳለ ። ጌታ ኾይ ብሎ የኢየሱስን ጌትነት በመንግስትኽ ብሎ መንግስቱ የማታልፍ ዘለዓለማዊነቷን አምኗል መስክሯል ። " መንግስቱ ዘለዓለም ወምኵናኑኒ ለትውልደ ትውልድ እንዲል። ለቁመተ የማን ያለሽ " ንዑ ኀቤየ " የአባቴ ብሩካን ወደ እኔ ኑ የሚለውን የሕይወት ቃል ነው። ፍቺው ከአሚን ያለሽ አሚን ማለት እሙን ማለት ነው። የታመነ ነው። አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት እንዳለው ከዚኽ የማይወጣ ነው። የተገለጠ እውነት ነው ይኽን የተገለጠን እውነት አዎን እውነት ነው ብለው ሊቀበሉት ተስፋም ሊያደርጉት ይገባል እያለሽም ነው ። ንባቡ በጎ ፍቺው እሙን ።
Oct 05, 2024