ሰላም ለሁላችሁ ይሁንና ሀሳባችሁን በቅንነት አካፍሉኝ። ፍቅረኛዬ አንድ ቀን ልጅ እንዳላት ነገረቺኝ። ከሷ ጋር መቀጠል እንደምፈልግ እና እንደማልፈልግ ጠየቀችኝ። እኔ አብሪያት ብቀጥል ደስ ይለኛል ግን ደግሞ ለልጇ ፍትዊ አባት( አንዳንዴ በልጆች መካከል የምረጥ አስገዳጅ ሁኔታሲያጋጥም ለማለት ነው) መሆን ባልችልስ ብዬ እፈራለሁ። የዛኔ ፍቅሬን፣ቤተሰቤን ሁሉንም ነገሬን ባጣስ የሚል ፍርሀት ይሰማኛል። እና ግንኙነቱን ለመቀጠል ወይም ለማቋረጥ መወሰን አልቻልኩም። እህት ወንድሞቼ እናተ ብትሆኑ ምንታደርጉ ነበር? በቅንነት መልሱልኝ። ለምታደርጉት በጎነት ሒዎት ትክፈላችሁ አመሰግናለሁ።
Oct 04, 2024ቀጥል አታቁም ፣ ልጅቷንም እንደ ልጅህ አሳድጋት መልካም ሂወት እመኝልሀለው
Oct 04, 2024