የወሲብ ማነቃቂያ መድሀኒት (ቪያግራ) ያለ ሀኪም ትዕዛዝ የወሰደው ግለሰብ ለአይነ ስውርነት ተዳረገ የ32 ዓመቱ ኢራናዊ የወሲብ ማነቃቂያ ወይም ቪያግራ የተሰኘውን መድሀኒት አብዝቶ በመውሰዱ ምክንያት እይታውን አጥቷል ተብሏል። እንደ ዴይሊሜይል ዘገባ ስሙ ያልተጠቀሰው ኢራናዊ ከህክምና ትዕዛዝ ውጪ ከመጠን በላይ በመውሰዱ ምክንያት ማየት እንዳልቻለ ተገልጿል። ግለሰቡ 100 ግራም መጠን ያለው ቪያግራ መድሀኒት በወሰደ ከ3 ሰዓት በኋላ የቀኝ አይኑ ማየት ማቆሙን ተናግሯል። © አል ዓይን @Amazing_fact_433 @Amazing_fact_433
Oct 21, 2024