Please 🙏 🙏 🙏 Ye 2017 matric mech endehone yemiyak kale. Share any information you have🫴
Sep 29, 2024#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር መተግባር እንደሚጀምር ተሰምቷል። በትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተፃፈ ደብዳቤ ተመልክተናል። ደብዳቤው ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣ እና ትክክለኛ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደብዳቤው ከደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አረጋግጧል። ደብዳቤው ከ2017 ትምህርት ዘመን ጀምሮ ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተግባር እንደሚጀምር ይገልፃል። በዚህም፦ - የ1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ፦ መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም - የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 9 እና 10/2017 ዓ.ም - የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይጀመራል። የ2017 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 27 ድረስ ይሰጣል። (ሙሉው የ2017 ትምህርት ዘመን የአካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል።) ምንጭ ➡️ @tikvahuniversity
Sep 29, 2024