ስልክሽ ጠፍቶበት ከነበረ አኹን እንዴት አገኘው። እስኪ ጠይቂው እኔ የጠፉብኝ ስልክ ቁጥሮች ስላሉ ይረዳኛል። የኾነው ኾኖ የደወለልሽ ሊመጣ ስለኾነ ነው። ያው ሲመጣ ደግሞ ያው ዲያስፖራ አይደለ ከተገኘ ድንግል ካልተገኘም የተገኘውን ነካክቶ ለመመለስ ዓላማዬ ብሎ የሚመጣው ብዙ ነው። ሊመጣ ሲል ቁጥርሽን ማግኘቱ ለዚኹ ዓላማም ይኾናል። 27 ዓመትሽ ነው አታማርጪ ምናምን የሚል የጓደኛ ግፊት የታከለበት ግንኙነት ስኬታማነቱ እምብዛም ነው። ከተሳሳተ ትዳር የዘገየ ትዳር በእጅጉ የተሻለ ነው። ትክክለኛው ሰው ቢኾንስ ያልሽበት ምክንያት አልታየኝም ! ! ዘ አሜሪካ መውሰዲንግ ወሬ እኔ አይጥመኝም በግሌ። ( በብዙ ምክንያቶች )
Sep 23, 2024