ጠንካራ እንደሆንክ ከፁሕፉህ ተረድጃለው። እግዚአብሔር የሚያደርግልን የምንፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገንን ነው እና በእምነት ቶሎ መወሰን ጥሩ አይደለም። እግዚአብሔር ትናተን ያኖረህ፣ ዛሬን ከእንቅልፍህ ያነቃህ ፣ የነገህ ተስፋህ እና የሚገባህን የሚያደርግልህ እርሱ ነው። ✍🏼ነገሮችን ከአለው ነባራዊ ሁኔታ ዛናገናዝብ ከመጠን በላይ መጠበቅ እንዲህ ያለ ስሜት እንዱሰማህ ያደርጋሉ። ነገሮችን ሊሳኩም እንደማይችሉ ማሰብ ጥሩ ነው። ሁሌም ቢሆን Plan B መኖር አለበት። ✍🏼 እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ለወደፊት ህይወትህ ጥሩ ነው። ምክንያቱም ምናልባት ከእዚህ የከፋ ነገር ሊያጋጥምህ ቢችል እንዴት መቋቋም እንዳለብህ እየተማርክ ነው። ሁሉም የሚማረው ካለመሳካት እና ከመሞከር ነው። ✍🏼ህይወት ⬇️⬆️⬇️⬆️⬇️⬆️ ናት። ሁሌም ወድቀህ እና ተነስተህ አትቀርም። ✍🏼አንድ ነገር ስትሰራ እስኪሳካ ድረስ ለሰው ብዙ አታውራ ። ሰውም እንዲጓጓ ማድረጉ ጥሩ አይደለም። ዝም ብለህ ስራ ከተሳካ ያእኔ አብረውህ ይደሰታሉ ካልተሳካም ወደ plan B ትሄዳለህ። አሁን አንተ እያስጨነቀህ ያለው ቤተሰብ ብዙ ነገር እየጠበቀ ነበር የሚለው ነው ። ለቤተሰብም ቢሆን ላይሳካ እንደሚችል ማሳወቅ ጥሩ ነው። ✍🏼ሁሌም ቢሆን የሆነ ነገር ከመጀመርህ በፊት ሰለእዛ ነገር የመሳካት እድሉ፣ የሚያስወጣህ ወጪ እና ስለምታገኘው ጥቅም በደንብ ማወቅ አለብህ። ያንን ነገር እስካላወከው ድረስ ቶሎ አለመወሰን ። ✍🏼መጨነቅህ ለምንድ ነው? ወይስ አሁንም የመሳካት እድል አለው? ካለው የሚያግዝህ አካል ካለ አናግር። ካልሆነ ግን ነገሩ አልፏል፤ አንተ በመጨነቅህ ምንም 🤷♂የምትለውጠው ነገር የለም ። ሰው እስከሆን ድረስ ነገሮች fail ሲያደርጉ መጨነቃችን ግድ ነው ግን ነገሩን እንደማትቀይረው ካወክ ከእዛ ነገር ቀስ እያል መራቅ ግድ ነው። ✍🏼ይህወትህ የሚቀየርበትን ሰዓት፣ ደቂቃ፣ ሰከንድ እና ማይክሮ ሰከንድ አታውቅም እና ሁሌም ቢሆን ተዘጋጅተህ ጠብቅ ። ትምህርትህን በደንብ ተከታተል የአንተ ህይወት የሚቀየረው እና የምትፈልገው ሰው መሆን የምትችለው አሁን የምትማርበት ዩንቨርሲቲ ሊሆን ይችላል። የተሻለ grade ለመስራት አቅደህ ተንቀሳቀስ እና ይህን ንዴትህን፣ ቁጭትህን ተጠቅመህ ነገ ደረትህን ነፍተህ የተሻለ የትምህርት እድል ልታገኝ ትችላለህ። ሁሌም ዝግጁ ሁን። ✍🏼የደካሞች ምርጫ ሁሌም የሆነ ነገር ሲፈጠር መሸሸኪያ መፈለግ ነው። አልኮል መጠጣት ከጀመርክ አንተ ደካማ ነህ፣ አንተ ተሸንፈሀል፣ አንተ እራስህን እቢራ ጠርሙስ ውስጥ ከተሀል። ሁሌም ቢሆን አትሸነፍ ጠንካራ ሁን። ✍🏼 ሁሌም ጠዋት ፀሎት አድርግ። መዝሙሮችን አዳምጥ፣ ከመፅሐፍ ቅዱስ መፅሐፈ ምሳሌ እና መክብብ አንብበው ። ደስ የሚልህ ነገር አድርግ፣ ስፖርት ስራ፣ ከሰዎች ጋር እረጅም ጊዜ አሳልፍ ስሜቱ እስኪለቅህ።እንደዚህ አይነት ነገር አጋጥሟቸው እንዴት እንዳሳለፉት የተለያዩ ሰዎች የተጡት ቃለ መጠየቅ ማየት። «በእግዚአብሔር ሁሌም ተማመን።» «ጥሩ እንዳለም መጥፎ መኖሩን አስብ።» «ሁሌም ተዘጋጅተ ጠብቅ » «ሁሌም plan B ይኑርህ።» «ሁሌም ስለምታደርገው ነገር እውቀት ይኑርህ።» 👌«ነገ ከዛሬ የተሻለ ነው።»
Sep 18, 2024