ሰዎች እዚህ ምድር ላይ ስራ ሰርቶ ለመኖር በጣም ተቸገርኩ ምንም ሊሆንልኝ አልቻለም የት ልሂድ ... እስካሁን ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም የተለያየ ቦታ ሰርቻለሁ .. ከኛም ቤተሰብ ውስጥ በጣም ይሆንላቸዋል አዲስ ነገር የመልመዱን የሚያቁትንም ስራ በመስራት በጣም ስኬታማ ናቸው...ሰው ከሰው አይነፃፀርም ነገር ግን እንዴት ሰው ከአለም ህዝብ ተለይቶ እንዲህ ይሰቃያል ... እኔ ያገኘሁትን እድል ሌሎች ቢያገኙ ምን ያክል ስኬታማ እንደሚሆኑ ሳስብ ይገርመኛል .. ለእኔ ብቻ የተዘጋ ነው እስክል ድረስ ተስፋቆርጫለሁ። ሌሎች ስራዎችንም የመሞከር ፍላጎቱ የለኝም ስራ መስራት እፈልጋለሁ ግን 1 ቀን ተሳክቶልኝ የልቤን አድርሼ አላውቅም። ሙያ ችሎ የሚያለምጥ ወይ ስራ የማይሰራ ወይ የማያሰራ ሰው ስመለከት ልቤ ይሰበራል እኔ እንደሱ ብችል...🤔 ብዬ እሩቅ አስቤያለሁ ... በአሁኑ ሰዓት እንደኔ ተስፋ የቆረጠ ሰው የለም። ደህና እየሄደለኝ ያለ ስራ ካለ ስልጣኑና ሀይሉ ያላቸው ሰዎች ባዶ እጄን ያስቀሩኛል...አቤት የምልበት ቦታ አላገኘሁም ደከመኝ ላውራው ብዬ እንጂ መፍትሔ የሌለውን በሽታ እንደማስታምም አውቃለሁ
Sep 17, 2024ዓለም የፈተና ቦታ ናት ! በስራ ቦታም ኾነ በየትኛውም እርምጃኽ ውስጥ በሚኖርኽ የሕይወት መስተጋብር መፈተን የግድ ነው ! ምድራዊያን አዳማዊያን ውጊያችን ሥጋና ደም በለበሱት ጥላ በተገለጡት ሥጋና ደም ከሌላቸው ሰማያዊያን ጋር እንደመኾኑ ያለ ፈተና መኖርን አታስበው አትመኘውም። እየተፈተነ ያልኾነ እርሱ እየኖረ አይደለም ! እግዚአብሔርን ዘወትር በፊቴ አየዋለው በቀኜ ነውና አልታወክም ! በልዑል መጠጊያ የሚኖር ኹሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝ የለም ከአንተም በቀር ረዳት የለኝም እያልክ እግዚአብሔርን ብቻ ይዘኽ ፈተና ኾኑብኝ የምትላቸውን ሰዎች ሳትፈራ ተጋፈጣቸው ! ! ከእግዚአብሔር በታች ለራስ ራስኽ ነኽ ያለኸው ማንም መጥቶ ስለ አንተ አይዋጋልኽም ! ስለ አንተ ከአንተ በቀር ማንም የለም ! ሥልጣኑ ኃይሉ አላቸው ያልካቸው ሰዎች ባዶ እጅኽን ሲያስቀሩኽ አልያም ያስቀሩኽ ሲመስልኽ አታለቃቅስ ተስፋ ለመቁረጥም አትዳዳ ምድራዊውን ሳየወኾን ሰማያዊውን ባለሥልጣን ተገን አድርገኽ መንድኽን ለእሱ አደራ እየሰጠኽ ደግሞ ተዋጋ አንድ ቀን እነዚኽ ሰዎች ደጅኽን እንደሚጠኑ እመን። መስተበቅል አምላክ ኹሉን ይበቀላል። ታገስ ! ! ዝም ብለኽ ግን ቁጭ አትበል ! ! ያው በዚኽ ውስጥ ሕመምህን ሳያዩና ሳያውቁ የሚያሙኽ ሰዎች ሐሜት ስላቅ ምጸት ሽሙጥ ያደማሃል ! ያማርርሃል እንደ ኢዮብ ጓደኞች እና እንደ ሚስቱ ይኾኑብሃል ! ይኽ አበሳጭቶኽ ግን ዓላማዬ ብለኽ ከያዝከው ፈቀቅ አትበል። ከሕይወት ተሞክሮ ነው የምነግርኽ ! ወደ ፈጠረኽ አምላክ ብቻ አቤት በል ጩኸትኽን ይቀሙሃልና ከምድር ጩኸትኽን የሚሰማ አትፈልግ ! ዝም ብለኽ ታገል ! ! Mark my word ሳናሸንፍ አንሞትም ! !
Sep 18, 2024