ሰላም ቤተሰብ? ጥያቄዬ አሁን አብሬዉ ያለሁት ልጅ ከበፊት ሴት ጓደኞቹ 2 ጊዜ እንዲያስወርዱ ያደረጋቸዉ ልጆች እንደነበሩት ነግሮኛል። ሰካራም ሱሰኛ ክለብ የሚያነጋም እንደነበር እና አሁን ተለዉጫለሁ ህይወት ቀይሮኛል ነዉ የሚለኝ። ለምን ልጅ በማስወረዱ ሀሳብ እንደተስማማ ስጠይቀዉ ከአንዷ ጋር በሀይማኖት አንድ ስላልሆኑ እና ሌላኛዋ ደሞ ቀድሞ ልጆች ስለነበራት አለኝ። ምንም ዉስጤ አልተቀበለዉም ሰማሁት እንጂ። እሱን ያገኘሁት አባቴ ሊሞት ሳምንት ያህል ቀደም ብሎ ነበር እና ሀዘን ላይ ስለነበርኩ ተጣበኩበት መሰለኝ። አሁን ወደ እራሴ ስመለስ ማሰብ ጀመርኩ። 32 አመቴ ነዉ ማግባት እና መዉለድ ብፈልግም እኔ እራሴን በብዙ ነገር ያስተካከልኩ እና ስርዓት ያለኝ ሴት ነኝ። ይህ ሰዉ ይገባኛል እስኪ ምከሩኝ? እሱ አሁን አሜሪካ ነዉ ያለዉ ወደፊት የምንኖረዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደሆነ ተነጋግረናል። እኔ ግራ የገባኝ ወንዶች ሌላዋን አስወርጂዉ ብላችሁ ልጅ ደሞ ከሌላዋ የምትፈልጉበት ጊዜ አለ? እኔንም አስወርጂዉ እንዳይለኝ ሰግቼ ነዉ።
Sep 06, 2024Stagebiw mnm neger wst endatgebi
Sep 06, 2024