selam endet nachu.. menm neger madreg yemalchlachew tnshm hone telk negeroch lay mechenek makom endet echlalew..... lelaw demo smetawi neg betnsh neger sazen tolo embaye yemetal mnamn ena ene demo endeza mehon alfelegm yersaen chegeroch berase meftat le bechaye tenkara mehon efelegalew andande arif yalhone mood lay behonm gn tolo wedebefitu lememeles endet echlalew ...ahun lay mnm tesfa maregew neger yelem ena erase lerase tenkara lemhon ena le family lewedefit cheger endalhon mitekemgen neger mekerug ahun 19 yr yemolagal ena tlk sew eyehonku nw ena endet strong mehon endemechl ke edmem ke hiwotm ketemarachut share argug kasfelegem tenker yale kal tetekemu 😄becha yehone energy miseteg neger awrug hasaben sleterdachug amesegnalew😘
Sep 05, 2024«ተስፋ ስላለሽ ነው ይህን የጠየቅሽው» አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሮ ለነገሮች ትኩረት ስሊሚሰጡ ትንሹንም ነገር በማግዘፍ የመጨነቅ ባህሪ አላቸው። እንደዚ አይነት ነገሮችን ለመተው ወይም ለመቀነስ እራስን በእውቀት ማዳበር እና ከእልምድ ይመጣል። ማድረግ ያለብሽ ነገር ✍🏼 አንዳንድ ነገሮች አሉ በመጨነቅ መቀየር የማችላቸው ፤ እነሱን መለየት ለምሳሌ፡ ስልክሽ ቢሰበር በመጨነቅ አይፈታም በማስጠገን እንጂ። ጭንቀት በመጠኑ ለሰው ልጅ ያስፈልገዋል፤ ሲበዛ ግህ ህመም ስለሚሆን በመጠኑ ይሁን ✍🏼 እራስን በእውቀት ማጎልበት። የእተለያዩ መፅሐፎችን በማንበብ ነገሮችን እንዴት መቋቋም እና መፍታት እንደሚቻል ማወቅ። እንዲሁም የተለያዩ ሴኬታማ የሆኑ ሰዎች የህይወት ታሪክ ማንበብ ጥሩ ነው። ✍🏼 አሁን ባለሽበት የትምህርት ወይም የእድሜ ደረጃ ማወቅ ያለብሽን ነገር ማወቅ። ለምሳሌ 12 ክፍል ብተሆኚ ለእንትራስ ፈተና የሚያበቃሽ እውቀት መያዝ ለነገው ይህወትሽ ወሳኝ ስለሆነ የመጨነቅ እድልሽ ይቀንሳል። ✍🏼 በእቅድ መመራት። እቅድ ልክ እንደ GPS ነው ። መድረስ የምትፈልጊበት እና ማሳካት የምትፈልጊውን ነገር ዲያሪ ላይ ፃፊው እና እሱ ለአንቺ GPSሽ ነው ። ስታቅጂ ባለሽ እውቀት እና ገንዘብ ላይ ተመስርተሽ ነው። ከሌለሽ እውቀት እና አቅም በላይ ማቀድ የመሳካት እድሉ ዝቅተኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ተስፋም የሚያስቆርጥ ስለሚሆን። ✍🏼 አመስጋኝ ሁኚ።ጤናሽ የአንቺ ተስፋሽ ነው። ጠዋት ከእንቅልፍሽ በጤና መነሳት ትልቅ ነገር ነው። ይህን ያላገኙ ብዙ ሚሊዮን ሰዎች አሉ ✍🏼 በሀይማኖትሽ ፀሎት/ዱአ ማድረግ። ፀሎት ማድረግ ለሰው ልጅ ትልቁ እና ትልቁ ነገር ነው። 📍 ይህን አስታውሽ የአንቺን እድል ያላገኙ ብዙ ሰዎች አሉ። መንገድ ላይ ዝናብ እና ፀሀይ እየተፈራረቀባቸው፣ ስለ ነገ አይደለም ስለ ዛሬ ምን እንደሚበሉ የማያውቁ አሉ፤ እነሱ ምን ተስፋ አድርገው ነው እየኖሩ ያሉት? ተስፋ ሁሌም ቢሆን አለ ግን ነገሮችን የምናይበት አንግል ነው የሚለያየው። ጤነኛ መሆንሽ ነገ የተሻለ ነገር እንደምሰሪ፤ ይህ « ተስፋ» ነው ........ መፅሐፍ አንብቢ በሶፍት ኮቢም በሀርድ ኮቢም
Sep 06, 2024