Hello guys ዛሬ አንድ ነገር ላማክራቹ እና ሀሳባቹን እንድትሰጡኝ ነበር። እቤት ውስጥ አብራቹ ያደጋቹትን ሰው ጠልታቹ ታቃላቹ? ማለት እኔ 19 አመቴ ነው እና 31 የሞላት እህት አለኝ። እና አሁን ጭራሽ ላይኔ ነው ያስጠላቺኝ።ከሙሉ ቤተሰብ ጋር ነው ምትኖረው እኔንም ጨምሮ ግን 31 አመቷም አይመስልም። ሲበዛ ግድ የለሽ እና ሰነፍ ናት በጣም ሲቀጥል ለወላጆቼ ራሱ ቅንጣት ታክል ነገር አርጋ አታውቅም። ቤት ውስጥ ምሳ ከሌለ ትዝ አይላትም እኔ ነኝ ሁላ ምሰራው።ወላጆቼም ሁሌ እንዳዘኑ ነው። የገቢ ችግር ነው እንዳልል ራሷንም ከራሷ በላይም ሚሆን ገንዘብ ታገኛለች። እና በቃ ከጊዜያት ቡሀላ በታምር እንዳታናግሪኝ ሁላ ብያት አናወራም። ከልቤ ነው ያስጠላቺኝ። እና እኔ ክፉ ሁኜ ነው? የኔ ልብ ነው የተሳሳተው ወይንስ እናተም አጋጥሟቹ ያቃል?
Sep 03, 2024ፕሊስ አትጨክኚባት የንቃተ ህሊና ጉድለት ይኖርባት ይሆናል ወይም በተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች ሞራሏ ወርዶ ሊሆን ይችላል ፤ እና አካልሽ የአካልሽ ክፋይ ናትና ችግሯን አጥንተሽ ልትደርሺበት ሚገባው አንቺ ነሽ ፤ 31 ማለት እኮ ቀልድ አደለም የራሷን ቤተሰብ መመስረት የነበረባት ጊዜ ነው ፤ እና ሰዎች ተስፋ ሲቆርጡና ህይወት ስትጨላልምባቸው ሲበዛ ግድ የለሽ እየሆኑ ይሄዳሉ ፤ እና አስተውዪ እና አትጨክኚ
Sep 04, 2024