በህይወትህ ውስጥ ላንተ የሚስፈልግህን ነገር ምረጥ እና እሱን ብቻ በየቀኑ ስራ (ለትኩረት አሪፍ ነው።) እንዲህ free time ካለህማ life skillን መርጠህ ተንቀሳቀስ ለምሳሌ ስፖርት መስራት መፅሐፍ ማንበብ *(ትኩረት፣የህይወት ፀፀቶች(የዶክተር እዮብ) ፣ #ዘአልኬሚስት ይህን እንድታዳብር የሚያረጉ ፕሮግራሞች ላይ መሳተፍ አጫጭር ኮርሶችን በonline መማር አንተ የፈለከውን ትምህርት ... ደግሞ ራስህን ከሰው ጋር አታወዳድር ሁሉም በያላፈበት የህይወት መስመር ወይ ፈተና ነው የሚኖረው ... መጀመሪያ ራስህ ላይ ስራ ከዛ አንተ ሳትሆን ሰዎች ወዳንተ ይመጣሉ። ደግሞ የማንም ጓደኛ መሆን አይጠበቅብህም ። አሁን መቅደም ያለበት አንተ እና አንተ ብቻ ነህ። አንተ ራስህን ስታሳድግ ራሳቸውን የሚያሳድጉ ልክ እንዳንተ አይነት ሰዎች ይመጣሉ እና አብረሃቸው ራስህን ታሳድጋለህ። ይህም አንተ ስለፈለክ እንጂ ሰው ኖረ አልኖረ ያን ያክል አስፈላጊ ነገር አይደለም። እና ደግሞ የራስህን ገንዘብ የምትይዝበትን መንገድ ፈልግ..ስራ ብዙ ነገሮችን ይፈታል ። ሀላፊነት እንዲሰማህ መሪ እንደሆንክ ለራስህ ከለላ እንድትሆን ያደርግሃል። በርታ ✌️
Sep 02, 2024