Selam guys endet nachu please yemetaku melsulegn lemewesen chegrogn nw bezu guwadegnoche le sera wede Thailand hedew eyeseru nw ke hedu wede 5 wer honoachewal mechem hulachenem enakalen tayland wust men demisera be video call awrten neber misrut ye scam sera nw bewer 1500$ nw mikefelachew ena endayehut lifachew Arif yimeslal ena enem lehed eyasebku nw gen demo riskun ferahut behuala lela neger bifeteres bye lemewesen kebedegb risk wesje lehid weyis yikrebegn metaku sewoch men telalachu
Aug 31, 2024" እንደ ባሪያ ነው የምንታየው ፤ እባካችሁ ጭሁልን !! " - በማይናማር የሚገኙ ወጣቶች ማይናማር እና ታይላንድ ድንበር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የበየነ መረብ ማጭበርበር (Online Scam) ተግባራት ከሚፈጸምባቸው አንዳንድ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክቶችን በቴሌግራም እየተቀበለ ይገኛል። እነዚህ ቦታዎች ላይ በርካታ የሀገራችን ወጣቶች ያሉ ሲሆን " ታይላንድ እንልካችኋለን " በሚል የደላሎች ማታለያ ተታለው ነው በማይናማር የበየነመረብ ማጭበርበር (Online Scam) ላይ ተሰማርተው የሚገኙት። ስሜን አይገለጽ ያለ በስፍራው ያለ ወጣት ፦ " ለምን ስራ አላመጣችሁም ? ለምን አልሰራችሁም (የኦንላይን ማጭበርበር) ተብሎ ሰው ይታሰራል። እስር ቤት ይጣላል። እኔ ለምሳሌ 5 ቀን ሙሉ እስር ቤት አድሪያለሁ። ያለ ምንም ምክንያት ። ሽንት ቤት መሄድ የለም፤ ራስህ ላይ ነው የምትሸናው ፣ውሃ በግድ ያስጠጣሉ እምቢ ማለት አይቻልም ፣ የቁም እስር ነው ፣ መጮህ አይቻልም አፋችን ውስጥ ጨርቅ ይከታሉ በስነ ልቦና ሊጎዱን ነው ይህን ሁሉ የሚያደርጉት። እንደ ሰው አንታይም። በስነልቦና በጣም እየተጎዳን ነው። በሰንሰለት ይገርፋሉ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ ያደርጋሉ፣ መሬት ውስጥ በሚቅበር ሽቦ ይገርፋሉ እራቁት። ለዚህ ችግር አንደኛው መጠየቅ ያለበት የታይላንድ መንግስት ነው። የሱን ቪዛ መተን ነው ወደዚህ የመጣነው። አሳልፈው የሚሰጡን ከታይላንድ ነው። ከባንኮክ ከኤርፖርት መጥተው በመኪና ሲወስዱን ያውቃል መንግስት ። የምንሰራበት ሲም ካርድ የታይላንድ ነው። ዓለም ሁሉ እየተጭበረበረ ያለበትን ስራ በታይላንድ ሲም ነው የሚሰራው። እዚህ በካምፕ ላይ ያለው ቁሳቁስ ከታይላንድ ነው የሚመጣው ፣ ህንጻ የሚሰራበት እቃ ከታይላንድ ነው፣ መብራት እና ውሃም ከታይላንድ ነው፣ አልጋው ምኑ የታይላንድ ነው። ቻይናም ስለ ሁኔታው የምታውቅ ሀገር ስለሆነች ማናገር ይገባል። በቻይናውያን ድጋፍ የተሰመረተ ኩባንያ ነው ያለው። መጠየቅ ያለባቸው ታይላንድ እና ቻይና ናቸው። ማይናማር ለራሷ ላለፉት በርካታ ዓመታት እስካሁን ድረስ በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ናት። የኢትዮጵያ መንግስት ታይላንድን እና ቻይናን ይጠይቅልን። የኢትዮጵያን ዜጎች ነው እንደ እቃ ነው የሚጠቀሙት። ቁሳቁስ ሲመጣ እንኳን የሚያሸክሙን እኛን ነው። እንደ አህያ ነው የሚጠቀሙን። ክትባት ሲመጣ ለኛ አይሰጥም። ጥቅም የለንም። እንደባሪያ ነው የምንታየው። እየኖርን አይደለም። ተስፋም የለንም። እባካችሁ ጭሁልን ! " ብሏል። ሪፖርት፦ አንድ የተመለከትነው ሪፖርት በማይናማር ፣ ካምቦዲያ፣ ላኦስ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የኦንላይን ማጭበርበር (Scam) ላይ የተሰማሩ ሰዎች አሉ። ማፊያዎች በሚመሯቸው በነዚህ አካላት በየአመቱ እስከ 43.8 ቢሊዮን ዶላር ድረስ ይሰርቃሉ። በማጨበርበር ስራው ላይ የተሰማሩት ሰዎች እራሳቸውም የችግሩ የመጀመሪያ ሰለባዎች ናቸው። #ጥንቃቄ፦ " እጅግ ጠቀም ላለ ስራ ነው " እየተባለ ወደ ታይላንድ የምትሄዱ ጥንቃቄ አድርጉ። ስራው ምንድነው በሉ ፣ ከታይላንድ ውጭ እንደማትወሰዱ እርግጠኛ ሁኑ ፣ ዶክመንት ተፈራረሙ የሚልኳቹን ሰዎች ማንነት አጣሩ፣ ኤጀንሲ ይሁን ደለላ ማስረጃቸውን ሁሉ ያዙ። ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይደረስ ! #TikvahEthiopia #Myanmar
Aug 31, 2024