it is a question for young Protestants Have you ever kissed your boyfriend or girlfriend? Is this a normal thing to do? Please help me out
Aug 30, 2024ወንድሜ ከሕይወት ተሞክሮዬ ልምከርህ kiss ማለት deep and intimate የሆነ ስሜትህን የምትጋራበት ነገር ነው። ይኸውልህ ግልጽ የሆነ ቦታ አይደለም የምታደርገው በስውር ነው ያ ደግሞ ለሌላ ቀጣይ ነገር ያጋልጥሃል እኔ ከቸከሴ ጋር መሳሳም ችግር የለውም ብዬ የጀመርኩት ነገር ዝሙት ላይ ጥሎኛል በቃ ስትሳሳም ጥልቅ ስሜትና በዛ ሰዓት የምታስበው አብሮ መተኛት ነው። ያ ደግሞ አጋጣሚዎች ከተመቻቹልህ ለመውደቅ ያጋልጥሃል። ደግሞ የወሲብ ነገር የግድ PIV መሆን የለበትም መሳሳሙ ራሱ foreplay ነው ራስህን ሟሟቅ። ስለዚህ ካደረግህ ሁለተኛ ደግመህ አታድርግ አሊያ ለተከበረ ሰርግ እንዳትደርስ ያደርግሃል ። መጽሐፍ ቅዱስም 1 ተሰሎንቄ 4:3-5 NASV [3] የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው፤ [4] ደግሞም እያንዳንዱ የገዛ ሰውነቱን በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት እንዲያውቅ ነው፤ [5] ይህም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወተ ሥጋ ምኞት አይሁን። ነው የሚለው ወደዝሙት የሚጋብዝ ሰውን የሚያሰናክል ነገር ነው።
Aug 30, 2024