ሰዎች ሰላም ስራ ሀ ብዬ ከጀመርኩበት እለት ጀምሮ ከቦታው በትንሽ ነገር ከአሰሪ ጋር በመቀያየም ወይ በእነሱ ጥፋት ወይም በእኔ ጥፋት ስራ አቋርጬ እቤት እቀመጣለሁ የአሁኑ ግን የተለየ ነው። በሀቀኝነት ከመስራቴ የተነሳ የግድያ ሙከራ በማድረግ ከቦታው ሊያፈናቅሉኝ ሞከሩ ያንን አለፍኩ ስል አሰሪዬ ያለምንም ምክንያት ከቦታው አባረረኝ። አሁን አዕምሮዬ የሆነ ሰዓት ጣራ ደርሶ ነው የሚመለሰው...እነዛን ሰዎች ሳስባቸው ያሳዝኑኛል ደግሞ የሆነ ሰዓት ላይ ደህና አድርገሽ አሳብጃቸው ይለኛል ... እንዴት አድርገው ሊገድሉኝ እንደሞከሩ ደግሞ አዕምሮዬ በቅደም ተከተል ነገሩን ያመነዥገዋል .. የሚገርማችሁ የምሰራበት ቦታ እግሬ ከረገጠ በራሱ ቤቴ ጉንዳን በጉንዳን አይጥ በአይጥ ይሆናል...ያውም ሞቶ የሚነሳ ጉንዳን...ይህን እንዴት እንደምረሳ ብቻ ንገሩኝ በፍፁም ነው ያልቻልኩት ሀሳቡ ደጋግሞ እየመጣ እያስጨነቀኝ ያለው!!
Aug 27, 2024ፀበል ፀበል ፀበል
Aug 27, 2024