ProudWalrus34129.5
#technology
ሰላም, ቴሌብር አካውንቴን ለረጅም ጊዜ ከ 2 አመት በላይ እጠቀምበት ነበር ነገርግን ከ 5 ቀን በፊት ምንም ባልተፈጠረበት ጠዋት ስነሳ Suspend ሆኖ አገኘሁት 127 ስደውልም አካውንትህ suspend ተደርጓል እንዲያጣሩልህ ልከንልሀል እያሉኝ ይሀው 5 ቀን አለፈው ውስጡ ደሞ ከ 5000 ብር በላይ አለበት በጣም ቴሌብር ተጠቃሚ ነበርኩኝ ቀን በቀን ለብዙ አገልግሎቶች እጠቀምበት ነበር አሁን ለምን ዘጉብኝ? ለምንድን ነውስ የተዘጋበትን ምክንያት በግልፅ የማያሳውቁኝ ያለምንም ምክንያት ምንም ከወትሮው የተለየ ነገር ሳላረግ ለምን ይዘጋብኛል? ቴሌ በአካል ሄጄ ነበር ምናልባት የቴሌብር ስምህ ከመታወቂያ ስምህ ጋር ስለተለያየ ይሆናል ብለው ስሜን አስተካከሉልኝ ግን እስካሁን አካውንቴ አልተከፈተም ምንድነው ማድረግ ያለብኝ ምታውቁ ካላችሁ ተባበሩኝ አመሰግናለሁ
Aug 27, 20242 engagements