DuskParrot26108.5
#relationships
ሰላም:: ጥያቄዬ በ20ዎቹ መጀመሪያ ላገባቹ ወንዶች ነው:: እኔ 20 አመቴ ነው:: አባቴ በ23 አመቱ ነው የወለደኝ እናቴ ደግሞ በ16 ዓመቷ ነበር የወለደችኝ:: እናም እንደ እናት እና አባት ብቻ ሳይሆን እንደ ጓደኛ ሆነው ነው ያሳደጉኝ:: እናም በጣም ደስተኛ ነኝ:: እነሱም ደስተኛ ናቸው:: እናም በ 20 እና 21 አመታቸው ያገቡና ቤተሰብ መስርተው የሚኖሩ ወንዶችን ሳይ በጣም እቀናለሁ(በመልካም መንገድ):: በነገራችን ላይ የሴት ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም🤭:: እዚህ ውስጥ በጊዜ ያገባቹ ወንዶች ካላቹ - አንደኛ ይሄን ከባድ ውሳኔ እንዴት ወሰናቹ? - ሁለተኛ ደግሞ የሚፀፅታቹ ነገር ካለ ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል አመሰግናለሁ::
Aug 26, 202435 engagements