ጭንቅላትሽን ስለተቆጣጠረ ነው አሁን sex ብሎ የሚያስቸግርሽ .. የውለታ ጉዳይ ላይ ከሆንሽ ማለትም እሱ ላንቺ ወንድ የለም እስክትዪ ድረስ ላንቺ መልዐክ ሆኖ ታየሽ በምላሹ ግን የሚጠይቅሽን በሙሉ ማድረግ አለብሽ። የውልሽ የኔ እናት 1 መልዐክ የሆነ ወንድ ብቻ አይደለም እዚህ ምድር ላይ የተፈጠረው ገና ብዙ ያላየሻቸው መልካም ወንዶች አሉ..ነገርየው አንቺ ወደሽና ፈቅደሽ የምታረጊው ነገር ብቻ ነው። እንኳ ለእሱ ብለሽ ለሰው ብለሽ እስከዛሬ ድረስ ያደረገሻቸው እና የፀፀቱሽ ነገሮችን አስቢ ... የሱ አንቺን block ካደረገ በዚህ ጉዳይ ተዪው እንደማይሆን ነግረሽዋል የማትፈልጊውን ነገር እየደጋገመ የሚጠይቅሽ ሰው አንቺን ሊረዳ አይፈልግም ወይም ሊያይሽ እና እሺ ካልሺው ወዳንቺ ሊመለስ ነው። እዚህ ጋር ተጠምደሽም ሊሆን ይችላል.. የሁላችንም ሰዎች ችግራችን አንድ የፍቅር አጋር በህይወታችን ሲኖረን በቃ ያለ እሱ ማንም እንደሌለ እና በአዕምሮአችን ውስጥ ያለው ብቸኛ ፍፁም እና እውነተኛ አጋር አርገን እንስለዋለን። እና የሆነ ቀን ሲሄድስ? መልስ አለሽ?..ከዛ ደግሞ ሌላው ይተካል! ዞሮ ዞሮ ላንቺ የሚመችሽን ብቻ አርጊ እንኳን በግንኙነት ይቅርና ለሰው ብለን የምናረጋቸው ትንንሽ ነገሮች የእድሜ ልክ ፀፀት ናቸው። እሱን እንዳላጣ ብለሽ አንቺ ራስሽን እንዳታጪ .. አሁን አይመስልሽም ግን ያንቺን ምቾት ፍላጎት የሚያከብር ብዙ ስማርት ወንድ አለ። አሁን በአንቺ እና በእሱ መካከል የተፈጠረው ነገር እንደፈተና ይሁናችሁ..እሺ ብትዪው ካንቺ የሚያገኘውን ነገር አስቦ አይኑን በጨው አጥቦ ይመለሳል። እምቢ ብለሽ አይተሽዋል .. መቼም!!! .. አይንሽን ይክፈተው እሱ መድሃኒያለም
Aug 26, 2024