ሰላም ይህ ጥያቄ ለኘሮቴስታንት እህት ወንድሞቼ ነው።በቅንነት መልሱልኝ 1) አንድ ሰው የሚጠመቀው ትልቅ ከሆነ በኋላ ነው? ከሆነ፤ህፃን ሆኖ ቢሞት ድኅነት ይቀርበታል? 2) “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” — ዮሐንስ 6፥54 ይህንን እንዴት ነው የምትተገብሩት 3)“ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥5 ይህንንስ እንዴት ታዩታላችሁ በአምልኮ፣በፀሎት... ሰዓት ሴት አትሸፈንም በኘሮቴስታንት። አመሰግናለሁ።
Aug 24, 2024ጥያቄውን ካየሁት ቆይቷል ነገር ግን ከእኔ የተሻለ ሰው በደምብ አብራርቶ ይመልሰዋል ብዬ ስላሰብኩኝ ዘልዬው ነበር:: ተመልሼ ሳየው ስላልተመለሰ እኔ ልሞክረው ብዬ ነው:: 1. ጥምቀት ለድህነት ነው ብለን አናምንም:: በእኛ አስተምህሮ 5ቱ ሶላዎች(Sola) የሚባሉ አሉ:: 1 -በጸጋ ብቻ | Grace Alone | Sola Gratia01. “በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው።” ኤፌሶን 2፥5 (አዲሱ መ.ት) 02. በእምነት ብቻ | Faith Alone | Sola Fide “ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ፣ ሕግን በመጠበቅ እንደማይጸድቅ እናውቃለን። ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን እንጸድቅ ዘንድ እኛም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይጸድቅምና።” ገላትያ 2፥16 (አዲሱ መ.ት) 03. በእግዚአብሔር ቃል ብቻ | Scripture Alone | Sola Scriptura “ከሕፃንነትህም ጀምረህ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥15 (አዲሱ መ.ት) 04. • በክርስቶስ ብቻ | Christ Alone | Solus Christus “ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” ዮሐንስ 14፥6 (አዲሱ መ.ት) 05. ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ | For the Glory of GOD Alone| Soli Deo Gloria “ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።” ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት) 2. የጌታ እራት እንወስዳለን:: እንደየ አብያተ ክርስቲያናት ፕሮግራም ይለያያል:: እኔ አባል በሆንኩበት ቤተ ክርስቲያን ወር በገባ በመጀመሪያው እሁድ ስርዓቱን እንፈፅማለን:: 3. እኔ መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ሴት ልጅ ራስዋን መሸፈን አለባት በሚለው እስማማለሁ:: ነገር ግን አንዳንዶች በዚህ አይስማሙም ምክንያታቸው ደግሞ ትፅዛዙ በዚያ ጊዜ ለነበሩ ሰዎች ነው ብለው ያምናሉ:: ሌሎች ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶችን ያቀርባሉ:: አብያተ ክርስቲያናትም በዚህ ጉዳይ ውሳኔ ሲያስተላልፉ ሰምቼ አላውቅም:: ምርጫውን ለምዕመኑ የተውት ነው የሚመስለው:: የሚሸፋፈንም አለ የማይሸፋፈንም አለ:: ቤተክርስቲያን ግን ሁሉንም ታስተናግዳለች:: ጥያቄዎቹን መልሻለሁ ብዬ አስባለሁ ያልተመለሰ ወይም ግልፅ ያልሆነ ካለ ግን ለመመለስ ዝግጁ ነኝ:: አመሰግናለሁ::
Aug 25, 2024