ከሁለት አመት በፊት በድንገት ወደህይወቴ መታ መልካም ጓደኛዬ ሆነች ተቀራረብን ተግባባን እሷም ለማንም ወንድ ያልሰጠችውን ቦታ ለኔ ሰጠችኝ እኔም ከማንም ያላገኘሁትን ሙሉ ሴትነት ከሷ አገኘው የኔ እንደሆነች እርግጠኛ ስለነበርኩ ከሷ ጋር ምንም ነገር ማድረግ አልፈለኩም ብቻ ማፍቀሬን ለመናገር ቀን መጠበቅ ጀመርኩኝ በድንገት በፊት ጀምሮ ይወዳት ያስቸግራት የነበረ ልጅ በድጋሚ ወደ ህይወቷ ገባ ከዛም የሱ ባለመሆኗ መጥፎ ሱስ ውስጥ እንደገባ እና አሁን ላይ እሺ ካላለችው እራሱን እንደሚያጠፋ ነገራት በጣም ስስ እና ለሰው የምትራራ ስለሆነች እሱን ለማዳን ስትል እድል እንደምትሰጠው ቃል ገባችለት እሱን ለመውደድ እንደምትሞክር እና ሌላ ወንድ እንደማታይ ይሄንን ለኔ አርፍዳ ነገረችኝ እንደማፈቅራት ነገርኳት ግን ረፍዷል ቀድሜ ነግሪያት ቢሆን የኔ ትሆን ነበር አሁን ግን ቃል ይዟታል ልታጣኝ አትፈልግም እሱንም መጉዳት አትፈልግም እሷም መሀል ቤት ተሰቃየች እኔም ከምነግራቹ በላይ አፍቅሪያታለው የኔ እንደሆነች እንደማገባት እርግጠኛ ነበርኩ አሁን ላይ ምን ማድረግ አለብኝ ምከሩኝ?
Aug 24, 2024" ለማንም ወንድ ያልሰጠችውን ቦታ ለእኔ ሰጠችኝ " :- አይባልም ! ! በምንም እርግጠኛ መኾን አትችልም ! ለማን ምን አይነት ቦታ በልቧ እና በአእምሮዋ እንደሰጠች እሷ እና ፈጣሪ ናቸው የሚያውቁት ! ስለ ራስኽ ስሜት ብቻ እርግጠኛ ኹን ! ! እሷ እሺ ካላለችው ራሱን ያጠፋል ይኽን ላንተ አርፍዳ ነገረች :- ምንም የማይጥም ነገር ነው ። ( ይቅርታ ግን ) ምክንያቱም ከቀድሞ ከአንተ ጋር ሌላ አይነት ግንኙነትን ብትፈልግ ያንን ውሳኔ ከመወሰኗም ኾነ ለእሱ ቃለወ ከመግባቷ በፊት ፍቅርኽን እንድትገልጽላት መንገዶች ትከፍትልኽ ነበረ አልያም ላንተ ስላላት ስሜት በገለጸችልኽ ነበረ ። ልታጣኝ አትፈልግም :- ( እና ኹለታችኹንም ልታጫውት ነው የምትፈልገው ? ካልኾነ ወንድሜ ነኽ እያለችኽ ነው አለቀ መልመጥመጥኽን ትተኽ ኑሮኽን ኑር ) እየውልኽ ወንድሜ እኔ በውሳኔ አምናለኹ ! ውሳኔዬ የሚያመጣም ምንም ይኹን ምን እቀበላለኹ ። ከዚኽ አንጻር የምልኽ ፍቅርኽንም ባልገለጽክበት ወይም ምንም ባልጀመርክበት ኹናቴ ውስጥ አገባታለው ብለኽ እርግጠኛ መኾንኽ ስኅተት ስለነበረ ስኅተትኽን አምነኽ ተዋት ! !
Aug 24, 2024