Hey everybody This thing is making me wonder. Is there anyone who started online chat and develop feelings for each other. Malt ahun lay bzu tarikochen esmalw ezim siteyeku ayalew and experience aregem awkalw gn eski endza hono wedetdar yezelke or still abro yale sew ale. At the first place is the feeling true that u love someone just by chat. Betam selebzabgn nw mesemaw such stories. Specially all i read is girls complaining abt breakup or ignoranceso what do u say girls(guys also can answer)
Aug 22, 2024ከአስራ ሦስት ዓመታት በፊት ነበረ ሔዋንን የተዋወቅኳት ። ሔዋን በጠሩ ዐይኖቿ ውስጥ ጭምትነት የሚነበብባት የድሬደዋ ልጅ ነበረች። እኔ ደግሞ ተጫዋችና ድንጋይን ዳቦ ነኽ ብዬ የማሳምን የሸገር አዱ ገነት ልጅ ። የኹለታችን መገናኛ Waplog የሚባል ማኅበራዊ ድህረ ገጽ ነበረ ። ---- ( ሕጻናት እንደማታውቁት ርግጠኛ ነኝ Eskimi የሚባልም ነበረ 😁 ) --- በፎቶዋ ውስጥ ይነበብ የነበረው ውበት " ስቀሽ አስደንግጪኝ " ብዬ የመጀመሪያውን የጽሑፍ መልዕክት እንድልክ አስገደደኝ ። " እ ማለት " ስትል ምላሿንም ላከችክኝ። እንዲኽ ነበረ የተዋወቅነው ። ከዚኽ በኋላማ ማን ያቁመን ከምሽቱ በሦስት ሰአት ላይ በዛው ድኅረ ገጽ ላይ እየተገናኘን የቀን ውሎአችንን እናወጋ ጀመር ። ይኽ ጨዋታችን የማረካት ሔዋን ስልክ ቁጥሯን ልትሰጠኝ አላቅማማችም ነበረ። ከዕለታት በአንድ ቀን መርካቶ በሚገኘውና እነግድበት ከነበረው ሱቅ ውስጥ ኾኜ ምሳ ሰአት ላይ ደወልኩ ። አነሳችው ! እሷ :- ሄሄሄ ሎ እኔ :- ሔዋን እሷ :- አዎ ነኝ ! ማን ልበል ? እኔ :- ሚኪያስ ነኝ ! ! ! እሷ:- ትንፋሿ ተቆራረጠ ። ፍራቻ ድንጋጤ ደስታ በድምጸቷ ውስጥ ይስተጋባ ጀመረ ። እኔም ስለ እውነቱ በእጅጉ ደስ አለኝ ። ኩራትም ተሰማኝ ! ! ከዛ በኋላ ነበረ ከማኅበራዊ ድኅረ ገጹ ባሻገር በስልክ ማውራትም ኾነ መጻጻፍ የጀመርነው ። እውነት ለመናገር ሥራ በዝቶብኝ አልያም ሳልሰማው ቀርቼ ቴክስት ካልመለስኩ በቀጣይ የማስተናግዳቸው መልዕክቶች ጭንቀትን እና ቁጣን ያዘሉ ነበሩ ። በቃ ስልክ ከደወልኩማ እሷም ማልቀስ እኔም ማባበል ነው። እያሳጠርኩት ስሄድ :- መዋደዳችንን ያወቀው ክፉ አጎቷ ስልኳን ቀማት። በዚኽ ጊዜም በአክስቷ ልጅ ስልክ ትደውልልኝ እና እናወራ ነበረ። በጊዜው ኹለታችንም ጋር ልጅነት አለ የቤተሰብም ፈቃድም አስፈላጊ ነበርና እኔም እሷ ጋር እሷም እኔ ጋር መምጣት የማይታሰብ ነበረ። አንድ ቀን ግን እሷ ካለችበት አገር እንደምመጣ ቃል ገባኹላት። ክፉ አጎቷ በአክስቷ ልጅም ስልክ እንዳንገናኝ በማድረጉ ተለያየን ። የገባኹትን ቃል ግን መጠበቅ ነበረብኝና አቅሙን ሳገኝ ወደ ድሬ አቀናኹ ። አልነበረችም ! ! የደረሰችበትን ለማወቅ ስል አጎቷ በነጠቃት ስልክ የአጎቷን ልጅ አወራው እና እቀርበው ጀመረ ። ምንም የማይነግረኝ አይነት ሰው ሲኾንብኝ ጊዜ ፖሊስ እንደኾንኩና በዛ ቁጥር የተፈጸመ ወንጀል እንዳለ በመግለጽ የስልኩን ባለቤት የደረሰበትን እንዲያሳውቀኝ አስፈራራኹት ። ኋላም ወደ ውጪ እንደወጣች አረጋገጥኩ ። ከዛም በኋላ በደስታ የራሴን ሕይወት መኖርን ጀመርኩ ( ከረጅሙ በአጭሩ ) እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ፍቅር አለ ! ! መገኛው የትም ሊኾን ይችላል። ማኅበራዊ ድኅረ ገጽ ስለኾነ ኹሉ ነገር ውሸት ነው አይባልም። በአካል መቀራረብ የሚቻልበት ኹኔታ ካለም በአካል መገናኘቱ የበለጠ የተሻለ ያደርገዋል። KTV ላይ አንድ ስሙን የራሳኹት ኢትዩጵያዊ አካል ጉዳተኛ ጋዜጠኛ አለ ሚስቱን በፌስ ቡክ አውቋት ከውጪ ስትመጣ እዛው ኤርፖርት ውስት ለመጋባት የወሰኑ ። በፍቅር የሚቀልዱ አልያም ፍቅርሽንም የማይረዱ ግን ብዙዎች ስላሉ መጠንቀቁ መልካም ነው። በተለይ ጊዜው ከፍቷልና።
Aug 22, 2024