Selam sewoc በፊት የምሰራበት ስራቦታ አከባቢ በፍቅር አይን የምንተያይ ልጅ ነበር..ታሪኩ ረጅም ነው። ብዙም አልቀርበውም ነበር..ከዚህ ልጅ ጋር የአይን ፍቅር ሲይዘን ... አብሬው ከነበርኩት ሰው ጋር ልንለያይ የመጨረሻዎቹ ሰዓታቶች ላይ ነበርን..ነገር ግን የነበረኝን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ሳላቋርጥ ከዚኛው ልጅ ጋር መሞከር አልፈለኩም። ምናልባትም እረፍት ያስፈልገኝ ይሆን ብዬ አሰብኩ....እና አሁን ላይ ለብቻዬ ነኝ። የምሰራበትን ቦታም ለቅቄያለሁ ... የአይን ፍቅር ከያዘኝ ሰው ጋርም አንገናኝም ... ነገር ግን ስልክ ቁጥሩን እንደምንም ማግኘት ችያለሁ..ይቅርብኝ ከእርሱ ጋር ወይስ ልፃፍለት ላውራው ምናምን አንዳንዴ በአካል አንገናኝም በየቀኑ አላየውም ማለቴ ልጁ በእኔ በጣም ተሰቃይቷል የፈረሰ ግንኙነት ቢኖረኝም ልደርበው ስላልፈለኩ እሱን ችላ ባልኩበት ሰዓት ስራ በራሱ መስራት አልቻለም ነበር..እሱ ሲደብረው በጣም ሲያዝን እኔንም ይሰማኝ አዝን ነበር ደስ ሲለው የኔም ደስታ ወደርየለውም። እና አሁን ስራ ለቀቀች ብሎ ቢረሳኝ ብረሳው መልካም ነው ወይስ ምንላርግ?
Aug 21, 2024የትም ብትሄጂ አትረሺውም ሌላ ህይወት ውስጥ እንኳን ብትገቢ አትረሺውም ስለዚህ ያለሽ አማራጭ ልጁን ማውራት ከሆነ ሆነ ካልሆነም ይቆርጥልሻል ሌላ ህይወት ጀምሮም ቢሆን አታወቂም ስለዚህ እያብሰለሰልሽ ከምትኖሪና የተዘበራረቀ ህይወትን ከምታሳልፊ አውሪው ምንም ማለት አይደለም አሁን እኮ ላንቺ ብለሽ እንጂ የሱን ሁኔታ አታውቂውም ስለዚህ ፈጠን በይ ☕️☕️
Aug 22, 2024