ሰዎች እኔ የምሰራው ሱቅ ላይ ነው። እና አለቅየው የእቃውን ዋጋ በአካባቢው ከሚሸጡት ሰዎች አውርዶ ወይም በዝቅተኛ ዋጋ ነው የሚሸጠው...እኔ ደግሞ በዝቅተኛው ም ጠራው በከፍተኛው ሰዎች ሳይከራከሩ ይገዛሉ። ከኔ ጋር ያሉ ሱቆች እንኳ እቃቸው እንዲሸጥላቸው ደመቅመቅ ሲያደርጉ እኔ የማላደርግበት ቀን ይበዛል። የሚፈልጉት እቃ ባማረ ሁኔታ ውጪ ተዘርግቶ እያዩ እኔ ጋር ገብተው ገዝተው ይወጣሉ። እነርሱ ጋር በፈለጉት ዋጋ ቢስማሙም እንኳ ጨምሬ ስጠራ እሺ ብለው ገዝተው ይወጣሉ። እና እኔ ምንም መተት አላሰራሁም ግን በዛ አከባቢ ያሉ ሻጮች በየቀኑ ይፈታተኑኛል። sales ላይ ብዙ ፍቅርም መውደድም የለኝም። ያን ያክል አካብጄም አልሰራም ነገር ግን ውጤታማ ነኝ ለራሴ! በየቀኑ ጠዋት ሲመለከቱኝ ግራ ይጋባሉ በምግብ ሊመርዙኝ ሞክረዋል...ለህይወቴ እየሰጋው ወረቀት ለማግኘት ግን ህይወቴን ላጣ ነው። ይህን ስራ ያገኘውት በሰው ነው ስራ አጣው ... በየቀኑ የነጠላ ጥለት የሱቅ በር መክፈቻ ላይ ይታሰራል። ዳቦ ብዪ ተብሎ ይሰጠኛል በህይወት ዘመኔ 1 አንድ ቀን በላው ከዛ ሌባ መጣብኝ የተወሰነ ዘርፎኛል ...ይህን የሚያረጉ ሰዎች ከአለቅየው ጋር ግንኙነት አላቸው እና ቀን አፍዝዝ አደንግዝ እያበሉኝ በተለያየ መንገድ እየሰጡኝ ትፈዛለች ነቃ አትልም አስወጣት ብለው ያሙኛል ምን ላድርግ ሰዎች?
Aug 19, 2024ፀበል እርጪው ጠዋት ጠዋት ምንም ነገር ከነሱ አትቀበይ ምንም ነገር ጥለው ብታገኚ አደንግጪ አማትቢ ሰይጣንን በእምነትሽ ብቻ ነው የምታሸንፊው
Aug 19, 2024