ሰላም ሰዎች እንዴት ናቹህ??? እኔ ከ 1 ወር በፊት ትርፍ አንጀት አስወጥቼ ነበር yaw be surgery ነው እና በሳምንቱ ኢንፌክሽን ፈጠረና ስፌቱ ተነስቶ ለ 1 ሳምንት አሳጥቤ ድጋሜ ተሰፋልኝ አሁን ሁለተኛ ዙሩ ከተሰፋ 15 ቀን ሆኖኛል ግን ሙሉ ለሙሉ ሊደርቅ አልቻለም ማለት መጀመሪያ ሰሞን ትንሽ ደም ያወጣ ነበር እና clinic ስቀርብ መታጠብ አለበት አሉኝ ያው እንደመጀመሪያው ተከፍቶ ሳይሆን ከላይ ብቻ እየተጫኑ ፈሳሹን ያወጡታል አሁን እነሱም ከዚ በኀላ አትምታ እቤት ተንከባከበው ብለውኝ ነበር ግን አንድ ቦታ ላይ በቻ አልፎ አልፎ ስጫነው በጣም ትንሽ መግል ነገር ይወጣዋል አንድ ቦታ ብቻ ነው ትንሽዬ ናት እና እባካቹ ግራ ገብቶናል እራሴ መንከባከብ እችላለው ወይስ ድጋሜ ልቅረብ እና ምን ማረግ እንዳለብኝ አላውቅም ደሞ ምንም መድሐኒት እየተጠቀምኩኝ አይደለም የሚቀባ መድሐኒት የለውም??? Please doctoroch or balemuyawoch tebaberugn ebakachu
Aug 19, 20241ኛ) በጭራሽ የቁስል ቦታውን አትነካካ፣ ክፍት ቁስል ከcontamination በፍጹም የየጸዳ መሆን አለበት። 2ኛ) የእሽጉን ዳሮች ውሃ እንዳይነኩት ጥንቃቄ አድርግ። ይልቁንም የቁስል እሽጉን ዳርዳሩን በአዲስ ጓንት እና ንጹሕ ፋሻ ተጠቅመህ በአዮዲን ወይም አልኮል በየቀን ወይም ሁለት አጽዳ። (ጤና ባለሙያ Safe እንደሆነ ከነገረህ ብቻ) 3ኛ) ቁስሉ already ፋሻ በጤና ባለሙያ አማካይነት የተፈታ ከሆነ በአልኮል/አዮዲን ብቻ ቦታውን ማጠቡ በቂ ነው። ነገር ግን በአልኮል ባልተነከረ እጅ ቦታውን ባትነካካው ይመረጣል። 4ኛ) ሳምንት አይተህ መግሉ ላይ መሻሻል ካላየክ ተመልሰህ መጠየቁ የተሻለ ነው። ⚠️ - ይሄ ምክር እየሰጠኹህ ያለሁት ካየኋቸው የህይወት ልምድ በመነሳት እንጂ የጤና ተማሪ ወይም ባለሙያ አይደለሁም። ስለዚህ አንድ የጤና ተማሪ/ባለሙያ በዚ reply ሥር ማስተካከያ ከሰጠኝ፤ እንደ ጤና እውቀቱ እና ትምህርቱ መሰረት የሱ ሃሳብ more ተቀባይነት ይኖረዋል።
Aug 19, 2024