ሰላም ቤተሰብ 😊 እንዴት ወደ ንባብ ህይወት መቀላቀል ችላላሁ?(እንዴት አንባቢ ልሁን) እና ከ ምን አይነት መፅሐፍ ልጀምር ?....
Aug 18, 2024አጫጭር የፍቅር ልቦለዶችን በማንበብ ጀምር ንባቡ ስሜት ሰቶህ boring እንዳይሆኑብህ ያረግሀል።ለምሳሌ የአሌክስ አብርሃም መፅሐፍት አሉልህ እነ ከዕለታት ግማሽ ቀን ፣ዙቤይዳ እና ሌሎቹንም ብታነባቸው ትወዳቸዋለህ። ከረጅም ልቦለዶች ጀምራለው ካልክም እነ ሰመመን ፣ ፍቅር እስከመቃብር አሉልህ።btw ፍቅር እስከ መቃብር ጀማሪም ሆነህ አንብበው አንድ ትልቅ ቤተ መፅሐፍት ሞሉ ያነበበ ሰውም ሆነህ ብታነበው የማይሰለችና ብዙ እውቀት የምታገኝበት ነው ስለ ፍቅር ብቻ ሳይሆን፤ ስለ ክብር ፤ስለ ጓደኝነት ፤ስለ በዛ ዘመን ስለነበረው አስተሳሰብ እና ስርአት ፤ ስለ ነፃ ፍቃድ እና ሌሎችም ጉዳዮች ያነሳል መፅሐፍ ተራ የፍቅር ልቦለድ ብቻ አይደለም።ብቻ ይህን መፅሐፍ ስታነብ በ audio ቢሆን የተሻለ ነው በጣም ለዛ ያላቸው ሰው ናቸው የተረኩት።... በነዚህ መፅሐፍት ንባብህን ጀምረህ ከዛ በኋላ እነ ስብሃትን እነ አለማየሁ ገላጋይን አነ ባዐሉን እነ አዳምን እና ሌሎችንም እያማረጥክ ማንብብ ነው።መልካም ንባብ!!
Aug 18, 2024