ፍቅረኛዬ መጥፎ የአፍ ጠረን አለበት እየተሰቀቅሁኝ ነው ከእሱ ጋር የማወራው ጉንፋን ሁሉ የሚያስይዝ የአፍ ጠረን ነው ያለበት ብዙ ጊዜ ስንገናኝ ማስቲካ ነገር እሰጠዋለሁ በትንሹም ቢሆን ጠረኑን ስለሚቀይረው እናወራለን ይህን ነገር በግልጽ አውርተንበት እናውቃለን ጥርሱን በደንብ እንደሚቦርሽ ግን ሊለቅለት እንዳልቻለ ነው የነገረኝ እኔ በዚህ ምክንያት ላጣው አልፈልግም በጣም አፈቅረዋለሁ ግን እንዲህ አብረን ከቀጠልን እኔን የሳይነስ በሽተኛ ሊያረገኝ ነው ይህን በሽታ የሚያክም የጥርስ ክሊንክ ያለበት የምታውቁ ካላችሁ ንገሩኝና ላሳክመውና ፍቅሬን አብሬው ደስ ብሎኝ ልኑር።
Aug 18, 2024የሳቃችሁ እንጭጭ ሰዎች ጥርሳችሁ ይርገፍ😏😏 መቼስ ልጁ የጤና ችግር ሆኖበት እንጅ በወርቅ አልገዛውም አይደል😏 እህቴ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው ያነሳሽው። እስኪ ከእውቀትም ከልምድም ላካፍልሽና የምትችይውን አግዥው:- መጥፎ የአፍ ጠረን በዋነኝነት መነሻው በዋነኝነት ጥርስ(ድድ)፣ ወይም ምላስ፣ ወይም ጉሮሮ፣ ወይም አፍንጫ ውስጥ አልያም systemic disease (ጨጓራ፣ጉበት፣ስኳር...በሽታዎች ) ናቸው። ህክምናውም መንስኤዉን መሰረት ያደረገ ነው። ጥርስ እና ድዱ ላይ ችግር ካለ በእርግጠኝነት ታክሞ ወይም ተንቅሎ ይድናል። ጉሮሮው check ይደረግ tonsil stone እንዳይሆን በቀላል ማይልት ነጫጭ ነገሮች ካሉ ፈንቅሎ ማውጣት ነው ቀላል ነው። አፍንጫው ውስጥ ወይም ጉሮሮው በኩል ሳይነስ ምናምን ፈሳሽ ካለበት በአንገት በላይ ሀኪም ይታከማል። ሌላውና ዋነኛው ምክንያት ምላስ ነው። ምላሱ ነጭ ወይም ቢጫ ብቻ ከኖርማል ፒንክ ከለር ውጭ ከሆነ ችግሩ እዛው ነው ማለት ነው። በሆነ spoon ነገር ምላሱን ቧጥጦ ያሽትተው እና መጥፎ ሽታ ካለው እሱ ነው። ትንሽ ለህክምና የሚያስቸግረው ምላስ ላይ ያለው። ምክንያቱ ደግሞ ባክቴሪያዎቹ የራስቸውን biofilm ፈጥረው ስለሚደበቁ መድሃኒቱ ሰርፆ ገብቶ አይገላቸውም። ወደ መፍትሔው ስንመጣ ምላስን ጧትና ማታ በምላስ ማፅጃ በመቧጠጥ ማፅዳት ፣ ከአልኮል ነፃ በሆነ mouthwash ጠዋትና ማታ መጉመጥመጥ፣ ጥርስን ጧትና ማታ መቦረሽ፣ ሌላው ለመጥፎ የአፍጠረን ምክንያቱ በሆነ ምክንያት የአፍ መድረቅ ካለበት ነው። ለዚህ ደግሞ መፍትሔው የታሸገ ውሃ ይዞ አሁንም ቅድምም ጎንጨት ብሎ መጉመጥመጥ ነው። በመጨረሻ ቅድም የገለፅኩት ጨጓራ፣ስኳር...ምናምን በሽታዎች ያሉበት ከሆነ እነሱ ሲታከሙ አብሮ ይድናል። በመጨረሻ ምክር። የጥርስ ሐኪም እና የአንገት በላይ አሳይው። metronidazole የሚባል ለ5 ቀን ያህል ወስዶ ይሞክረው። therabreath የሚባል የmouthwash ይጠቀም። አንድ ቀን መፍትሔ ይኖረዋል አይዞሽ። .......(ጤና ባለሙያ ነኝ)
Aug 18, 2024