Betedegagami slemtsemut lelawn neger ltewew ena Be mlach meteltelun mn ametaw koy
Aug 17, 2024አንድ ሰሞን ተንጫጭታችኹ ለምትተውት ነገር አንድን ነገር ደጋግማችኹ በማንሳት የራሳችኹንም ኾነ የሌላውንም ሰው የአእምሮ ሰላም አታውኩ ። ( በዚኽ እና በመሰል ኲነቶች ብዙዎች ባልተገባ ኀዘን ራሳቸውን ወደ ማጥፋትና በአገራቸውም ተስፋ ወደ መቁረጥ ይገባሉና ) ከእልፍ ወሬ አንድ ተግባር የተሻለ ነው። ምንም ማድረግ ባትችሉ " ስለ ራሳችኹና ስለ አገራችኹ የእንባ መስዋትን ለእግዚአብሔር አቅርቡ " በዚኽ 7 እና 8 ወር ውስጥ ብቻ ወደ 11 የሚደርሱ የሕጻናትን መደፈር ተመልክተናል ! ሕይወታችንና ተግባራችን ግን ልቡ እንደተሰበረና እንዳዘነ እንዳልኾነ እሙን ነው ። የማስመሰል በሽታ ተጠናውቶናል ። የእግዚአብሔር መስዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነውና በተሰበረ ልቦና መኖር ብንችል ከምድራዊያን ያይደለ ከሰማያዊው ፍርድን ባገኘን ነበረ ።
Aug 18, 2024