ሰላም ሰዎች በፍቅር ግንኙነት በጣም በድሏቹ የሄደ እና ድንግልናቹን የወሰደ ሰው እንዴት ነው ከነ መፈጠሩ መርሳት ሚቻለው በፈጠራቹ እርዱኝ ምጠቁሙኝ you tube channal ካለም ጠቁሙኝ እባካችሁ 4 አመት ሆነኝ ስለሱ ብቻ ነው ማስብ::🙏🙏🙏🙏
Aug 17, 2024ከነመፈጠሩ መርሳት አትችይም ! ( በዚኽ አጋጣሚ የቻለ ካለ አንድ ሰው እኔ ይበል ) ረሳኹት ብለሽ አዲስ ፍቅረኛን ይዘሽ ለመኖር ብትጀምሪ እንኳን የድንግልናዋ ነገር መነሳቷ እንደማይቀር ኹሉ ዳግም እሱንም ማስታወስሽ የማይቀር ነው ። ( አንድም ለዚኽ ነው ሩካቤ ሥጋ ከትዳር አጋር ጋር ብቻ የሚኾነው ) የትውልድ በሽታ :- መልስ ፍለጋ ጎግል , ራስን ፍለጋ ዩቲዩብ አልያም አንድ አንድ ስልጠና ( ይኽ አይነቱ መንገድ ማደንዘዣ እንጂ መድኀኒት አይደለም ~ ማስታገሻ እንጂ መፈወሻ አይደለም ) የምጠቁምሽ :- በቅድሚያ ጸሎት ! በመቀጠል መንፈሳዊ መጽሐፍትን አንብቢ ! ( እነዚኽ ኹኔታዎችን እንድትቀበይ እና ከራስሽም ከፈጣሪሽም እንድትታረቂ ይረዱሻል )
Aug 18, 2024