ሁሉም እናቶች ግን ጥሩ ናቸው??ወይም ምናልባት የኔ እናት ብቻ ናት??የእርሷ ልጅ መሆኔን እራሱ እጠራጠራለሁ guess what ገንዘብ አላት ግን ልታስተምረኝ አትፈልግም። ታምሜ እንኳን ምንም ግድ አይሰጣትም ማሳከም አይደለም ተሻለሽ እንኳን ብላ አትጠይቀኝም። even የአባቴ ዘር እና የእርሷ ዘር ስለሚለያይ የዘርመንዘርሽ ችግር ነው (በዘር ሁላ ትሰድበኛለች) ታላላቄም ከቤት ወቶ ነው ሚኖረው። እኔ ግን የግቢ ተማሪ ነኝ እና ለbreak እራሱ ከእርሷ ጋራ መኖር ከብዶኛል ።አንዳንዴ ስትፈልጊ አግቢ ትለኛለች። ገና 20 አመቴ ነው። እና እራሴ ላይ መጥፎ ውሳኔ እንዳልወስን እየፈራሁ ነው።ምን ባደርግ ይሻለኛል ??
Aug 14, 2024መሳደብ እንኳን የአብዛኛዉ እናቶች ባህሪ ይመስለኛል እኔንም እናቴ በጣም ስትናደድ ትሞልጨኛለች ግን ይቅርታ ባትጠይቀኝም ተመልሳ ትተወዋለች:: እኔም በጣም እየተናደድኩኝ እንዴት እንዲ ትለኛለች ብዬ አስባለሁ ነገር ግን ከዚህ በኃላ አብሪያት የምኖረው ለጥቂት አመታት ብቻ መሆኑ እያሰብኩኝ ምንም እንዳልተፈጠረ እንቀጥላለን:: መለያየት ግድ የሚሆንበት ቀን እስኪመጣ እንንከባከባቸው:: እናቶቻችንምኮ ስሜት አላቸው ሲከፋቸው ሊቀያየሩ ይችላሉ ስለዚህ ልንረዳቸው ይገባል:: ሺ አመት አብረን አንኖር !
Aug 14, 2024