ሰላም ሁላቹሁም እንዴት ናቹ አሁን ላይ በጣም እየበዛ እና እያስተዋልኩት ያለሁት ነገር ምን መሰላቹ ብዙ ነገሮች ኖርማል ነው ብዬ ማሰብ ጀምሪያለሁ ለምሳሌ ከ lgbt የተገናኙ ነገሮች እና ይሄ ነገር ደሞ እኔን ብቻ ሳይሆን በጣም ብዙ ሰዎች ጋር ነው እና እስቲ ሀሳባችሁን አጋሩኝ ።
Aug 13, 2024ሰላም በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳብ የመስጠት አጋጣሚውን ስላገኘሁ ደስ እንዳለኝ በመግለፅ ሀሳቤን ላዋጣ! ልጆች እያለን ሰይጣንን ስናስብ ሁላችንም የሆነ አስፈሪ፣ ጭራቅ የመሰለ፣ ቀንድ ያለውና ጥቁር የለበሰ አይነት ምስል ነበር ወደ አዕምሯችን የሚመጣው፤ ለዛም ነበር የምንፈራው! አደግ እያልን አያ ጅቦ መጥቶ እንዳይበላችሁ ይሉን የነበረው ማስፈራሪያ ምንነት የገባን ቀን፣ አወቅን ብለን ያሰብን ቀን አያ ጅቦን መፍራት ተውን! አንዳንዴ ብዙ ማወቅ ወይም ስለነገርየው ደጋግሞ መስማት ይበልጥ እየቀለለን እንዲመጣ ያደርጋል! በቀደሙት ዘመናት በየሰዉ ሃገር ይህን ያህል ሰው በተፈጥሮ አደጋ አሊያም በጦርነት አለቀ ሲባል “እግዚኦ ሰውረን ከመዓቱ” እንዳላልን በዚህችው በእኛው ሃገር የሰው እልቂትን ደግመን ደጋግመን ስንሰማው ተላምደነው ቁጭ አልን! በጥያቄ ላይ ከተነሳው ጉዳይ ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ይመስለኛል! ስለ ግብረሰዶም ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ልጅ ሳለሁ መፅሀፍ ቅዱስን ስማር ነበር፤ የሰዶም እና ገሞራ ከተሞችን ጥፋት የሚዘግበውነ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍልን ሳጠና መሆኑ ነው። ያኔ የቀሰምኩት እውቀት አምላክ ይመስገን እስካሁንም ተፀይፌው እንድኖር አድርጎኛል! ሰይጣን ሰዎችን በማሳሳት ረገድ የ6,000 ዓመት የስራ ልምድ አለው! ፊት ለፊት እኔ ሰይጣን ነኝ ብሎም አይቀርብም! ይልቁኑስ ራሱን ሰውሮ የብርሃን መልኣክ በመምሰል ይቀርባል! በዚህ "Globalization" በተስፋፋበት ዘመን የነጮችን ያዘቀጠ እና እንስሳዊ ትምህርት ለማግኘት የግድ ‘ምን ይላሉ’ ብሎ ጥናታዊ ምርምር ማድረግ አይጠይቅም! በእጃችን በያዝነው ስልክ የተወሰኑ ቁልፎችን በመጫን ብቻ ማግኘት ይቻላል! ለምን ተለመደ ለሚለው በርካታ ምክንያት ማንሳት ይቻላል: 1) የማህበረሰብ መሰረት ተደርጎ የሚታየው ቤተሰብ ሥረ—መሰረቱ መናጋቱ ፦ ወላጅ ልጁን የስነምግባር እሴቶችን ከማስተማር ይልቅ ከኑሮ ጋር የሚያደርገው ትግል ላይ አተኩሯል! ስራ ውሎ ደክሞት ይመጣል ከልጁ ጋር ጥሩ የሃሳብ ልውውጥ አያደርግም ስልኩን ለልጁ ሰጥቶ እራቱን ቴሌቪዥን እያየ ይበላል አለቀ! የቴክኖሎጂ ተፅዕኖን ልብ ይለዋል! ልጁ ደግሞ ከኢንተርኔት ላይ የሚያገናቸው “መምህራን” ከባህልና እምነቱ ያፈነገጠ ትምህርትን ይሰብኩታል! ቤትም ሆነ ትምህርት ቤት አርዓያ አጥቶ ያደገ ከ ሃይማኖቱ ያፈነገጠ ትውልድ ለመሰል መርዝ ተጋላጭ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው! 2) የብልግና ምስሎች Pornography እንደልብ መገኘት በፊት መሰል ነገር ለማግኘት ፊልም ቤት ሄዶ መከራየት አሊያም መፅሄት መግዛት ይጠይቅ ነበር! አሁን ግን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል! ስልጣኔ ብለን የተቀበልነው ከነግሳንግሱ ነው እና ይህ አደገኛ ሱስ በሚያሳዝን ሁኔታ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ 8–15 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ልጆችን ይይዛል! አዕምሯችን fully develop አድርጎ ሳይጨርስ በመሰል እርኩስ ነገሮች እየተቀረፀ ይሄዳል፤ ከኮኬን ሱስ በማይተናነስ መልኩ ትውልዱን ሱሰኛ አድርጎ አሳስሮ ያስቀመጠ እውነት ጥናት ቢደረግ የሁላችንንም ቤት ያንኳኳ የክፍለዘመኑ ነቀርሳ ነው! 3) ጠያቂና አንባቢ ትውልድ እየጠፋ መሆኑ: የ Hollywood & Billboard እኮ ሆኗል ትውልዱን እየቀረፀው ያለው! ወደ ከተማ ወጣ ብላችሁ ወጣቱን የመመልከት አጋጣሚ ካገኛችሁ እስቲ በእኔ ሞት ልብ ብላችሁ አስተውሉ! ራሱንና ማንነቱን ያጣ፣ አለባበሱ፣ አረማመዱ፣ ፀጉር አያያዙ ፍፁም ውጪኛውን አለም የመሰለ ትውልድ ነው ብቅ እያለ ያለው! የውጪውን የፊልም ኢንዱስትሪ ግቱ ብለን ሳንጨርስ የሃገሬው ፊልምና መዝናኛ ኢንዱስትሪ ትውልዱን ምንድነው እያስተማረው ብሎ መጠየቅ ብቻ እኮ በቂ ነው! ስንት የሚነገር፣ ፊልምና መፃህፍት የሚወጣው ባህል፣ ታሪክና ትውፊት ያለን ህዝቦች ነጭ አምላኪ አድርገው ቁጭ አድርገውናል! ነጮቹ ጋጥወጥ ምግባራቸውን ሲያራግፉብን ሃይ ባይ አጥቶ በቦይ እንዳለ ውሃ በቀደዱልን እየፈሰስን ነው! እንጃ እኔ ለሃገሬ እፈራላታለሁ! ብቻ ልቦናና ማስተዋሉን ያድለን 😔🙏🙏🙏
Aug 13, 2024