ይህ ጥያቄ ለኖረበት ሰው ወይም ከዚህ ህመም አደጋ በብልህነት ላመለጠ ሰው ይሁንልኝ። ከማያልቁ ስቃዮቼ ውስጥ አንዱን ልንገራችሁ እናም በሃሳብ በፀሎት በጥበብ አግዙኝ። አሁን የምኖርበት ቦታ ለስራ ነበር የመጣውት እናም በባህሪዬ የሰው ነገር መንካትም ማስነካትም አልወድም። ሀቀኛ ወይም ታማኝ ከሚባሉ ሰዎች ውስጥ ነኝ። አሁን ያለውበት ቦታ እንደመጣው አንድ ስራ ጀመርኩ የስራ ቦታው ላይ ያሉ ሰዎች በጣም ሌቦች ከመሆናቸው የተነሳ ለዛ ስርቆታቸው የተመቻቸው ስላልሆንኩኝ እንዲሁ የሚሰሩትን ስራ እንኳን ማየት ፈልጌ ሳልፈልግ ይጋለጣሉ። ይህን መከራ እና ስቃይ ሌላ ራሴ ላይ መዘዝ ከማምጣቱ በፊት ከስራ ለቅቄ ወጣሁ። አሁን ያለሁበት ቦታ ም በተመሳሳይ ሁኔታ እኔን የሚጎዳ ሰው ተነሳ እንደውም የግድያ ሙከራ አደረገብኝ። ይህን ግን ማንም አያውቅም። እንደቀደመው ስራዬን እንዳለቅ ብዙ ሀላፊነት አለብኝ ኑሮውን አልችለውም። ተመልከቱ የእኔ ጥፋት መዝረፍ እና ማጭበርበር አለመቻሌ ነው? ይህ አለም ለእኛ አይሆንም ይለኝ ነበር አባቴ እናም ልክ ነው። ለሀቀኛ የሰው ነገር ለማይፈልጉ እና ሰይጣን ላልሆኑ ሰዎች ይከብዳል። እና ንገሩኝ ምንድነው ጥፋቴ...ይህን መልካም ያልሆነ ነገር የምታደርጉም ሰዎች ካላችሁ ለምን እንደሆነ እስኪ አውሩኝ...ከገዳዬ ጋር ነኝ ሁሌም አይኑን አየዋለሁ አቀፈዋለሁ ስመዋለሁ..ተመልከቱ ሀሳባችሁን አጋሩኝ 🙏
Aug 11, 2024በምድር ላይ ብቻህን ብትቀር እንኳን ሰዎችን ለሚጎዳ ተግባር ተባባሪ እንዳትሆን መስሎን ነው እንጂ ሁሉም አላፊ ነው ብርም ስልጣንም ንፁህ ህሊናህን ግን ሁሌም ይዘኸው ትጓዛለህ
Aug 12, 2024