ወንድሜ መከላከያ ተመዝግቦ እኛ ሳናውቅ 17 አመቱ ነው እና ከሁለት ወር በፊት የውትድርና ምዝገባ ጨርሰናል ብለው ያፈሱትንም ልከው ነበር 😭 አሁን እንደ አዲስ ጀምረው ነው አልገባኝም እሽ ወዴት ነው ሚመድብት እናቴ ልታብድ ነው እባካችሁ ምታቁትን ንገሩኝ
Aug 08, 202417 አመቱ ከሆነ may be ብላቴ ምናምን yehonal ሀዋሳ መሰለኝ ያለው ሌላ ደሞ ሽራሮ የሚባል ነው እሱ ደሞ ወደ ጎጃም ይመስለኛል ሌላ ቦታዎች አላቅም ስልክ የሚደውልበት አጋጣሚ ካለ እንዲጠፋ ምናምን ንገሩት ጦርነት ከላኩትም በሰላም እጁን ሰቶ እንዲመለስ አድርጉ ግን ከእናንተ ጋር ተጣልቶ ከሆነ የሄደው የመደወል አጋጣሚ እንኳን ቢያገኝ አይደውልም ከደወለ ግን የሆነ ነገር ፈልጎ ከልክላቹት ከሆነ እሱን ነገር እንደምታደርጉለት ንገሩት አብዛኞቹ እንደዛ ናቸው ብዬ ነው እግዚአብሔር በሰላም ይመልስላቹ 🙏
Aug 08, 2024